ስከርቪ በአመጋገብዎ ውስጥ ጉልህ በሆነ የቫይታሚን ሲ እጥረት ምክንያት የሚከሰት በሽታ ነው። ይህ ማለት ስከርቪ በከባድ ወይም ከፍተኛ የቫይታሚን ሲ እጥረት ሲከሰት የሚመጣ ነዉ።
የቫይታሚን ሲ እጥረት የሚከሰተዉ በቫይታሚን ሲ የበለፀጉ ምግቦችነ የማይመገቡ ከሆነ ነዉ።
ቫይታሚን ሲ (አስኮሮቢክ አሲድ) ለሰውነትዎ በጣም ጠቃሚ ንጥረ ነገር ነው። ቫይታሚን ሲ ለቆዳዎ፣ ለአጥንትዎና ለሰዉነትዎ ቲሹዎች እድገት፣ መጎልበትና ለመዳን አስፈላጊ ነዉ። በተጨማሪም ቫይታሚን ሲ የደም ቧንቧዎች በአግባቡ እንዲሰሩና ጥርስዎና ድድዎን ጤንነት ለመጠበቅ ይረዳል። እንዲሁም የብረት ማዕድን ከአንጀታችን እንዲመጠጥ ለመርዳትና በቃጠሎና በሌላ ምክንያት የተፈጠረን ቁስል እንዲፈወስ ያግዛል።
እስከርቪን እንዴት መከላከል ይቻላል?
በአመጋገብዎ ውስጥ የሚመከረውን የቫይታሚን ሲ ዕለታዊ መጠን በማግኘት ወይም በመመገብ የስከርቪ ህመምን መከላከል ይችላሉ።
የቫይታሚን ሲ ምርጥ ምንጮች ( በቫይታሚን ሲ የበለፀጉ ምግቦች) ትኩስ ፍራፍሬዎችና አትክልቶች ናቸው። ጥሩ የቫይታሚን ሲ ምንጮች የሚከተሉትን ያካትታሉ:-
· ፍራፍሬዎች ( በተለይ ብርቱካንና ሎሚ)
· ቲማቲም
· ድንች
· ያበባ ጎመን
· ስትሮቤሪ
· ቃሪያና ያመሳሰሉት ናቸዉ።