094 046 4646/0940 565656    
info@sainturaelclinic.com
Follow Us:

View Blog

የመገጣጠሚያ ህመም (አርትራይትስ)


የመገጣጠሚያ ህመም (አርትራይትስ)
ካለዎ ማድረግ ያለብዎትና የሌለብዎ ነገሮች
የመገጣጠሚያ ላይ ህመም ወይም አርትራይተስ በአለም አቀፍ ደረጃ ለህመምና ለአካል ጉዳት የሚዳርግ ዋነኛ መንስኤ ነው።
በየቀኑ ማድረግ ያለብዎ
ተቀምጠውም ሆነ ቆመው ወይም እንቅስቃሴ ላይ እያሉ ለመገጣጠሚያዎችዎ ትኩረት ይስጡ።
❤️ መገጣጠሚያዎችዎ እንዲንቀሳቀሱ ያድርጉ፦ በየቀኑ በቀስታ መገጣጠሚያዎችዎን በተሟላ ሁኔታ በሁሉም የእንቅስቃሴ አቅጣጫ ያንቀሳቅሱ
❤️ ገደብዎን ይወቁ፦የእንቅስቃሴና እረፍትን በሚዛን ያድርጉ፣ ከመጠን በላይ አይንቀሳቀሱ። የአኗኗ ዘይቤ ለዉጦችን ያድርጉ
❤️ ትክክለኛዉን የሰዉነት ፖስቸር ይጠብቁ፦ በትክክል እንዴት እንደሚቀመጡ፣ እንደሚቆሙና እንደሚንቀሳቀሱ ይወቁ።
❤️ የሰዉነት ክብደትዎን ያስተካክሉ፦ ከመጠን በላይ መወፈር የአርትራይተስ ችግሮችን ሊጨምርና ለአርትራይተስ ህመም አስተዋጽኦ ያደርጋል።
❤️ ማጨስን ማቆም፥- ማጨስ በመገጣጠሚያ ህብረ ህዋሳት ላይ ውጥረት ያስከትላል፤ ይህም የመገጣጠሚያ ህመምን ይጨምራል።
የአካል ብቃት እንቅስቃሴ
የመገጣጠሚያ ህመም ካለዉ ተገቢዉን የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ ህመምንንና የመገጣጠሚያ መድረቅን ( መጠንከርን) በመቀነስ የጡንቻ ጥንካሬን፣ የመገጣጠሚያ የእንቅስቃሴ አቅሙንና ጽናትን (ኢንዱራንስ) ለመጠበቅ ይረዳል።

ማድረግ ያለብዎ
ትክክለኛዎቹን የእንቅስቃሴ ዓይነቶች ይምረጡ- በመገጣጠሚያዎችዎ ዙሪያ ጡንቻዎችን የሚገነቡ ግን መገጣጠሚያዎቹን የማይጎዱ እንቅስቃሴዎችን ይምረጡ።
ስትረች (የመለጠጥ) እንቅስቃሴ ላይ፣ የመገጣጠሚያዉን ሁሉንም የእንቅስቃሴ አቅጣጫ የሚያስጠብቁና ቀሰ በቀስ እያሳደጉት የሚሄዱ ስትሬንግዝ እንቅስቃሴዎች ላይ ትኩረት ያድርጉ ።
ስሜትዎን ለማሻሻል እንዲሁም የሰዉነት ክብደትዎን ለመቆጣጠር በመገጣጠሚያዎ ላይ ዝቅተኛ ተፅእኖ ሊያሳድሩ የሚችሉ እንደ ኤሮቢክ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ፣ እርምጃ ( ወክ ማድረግ)፣ የዉሃ ዉስጥ እንቅስቃሴና ብስክሌት መንዳትን በእንቅስቃሴዎ ዉስጥ ያጠቃሉ።

ማስወገድ ያለብዎ
በመገጣጠሚያዎ ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖና ተደጋጋሚ እንቅስቃሴን የሚያካትቱ እንቅስቃሴዎችን ያስወግዱ፣ ለምሳሌ፡-
???? ሩጫ
???? ዝላይ
???? ቴንስ
????   ከፍተኛ ተፅእኖ የሚያሳድሩ ኤሮቢክ የአካል ብቃት እንቅስቃሴና
???? እንደ ቴኒስ ጨዋታ ያሉ ተመሳሳይ እንቅስቃሴዎች ያሉትን ደጋግሞ መድገም ማስወገድ ያስፈልጋል

አድራሻችን፦ ቦሌ ሩዋንዳ ከሩዋንዳ ኤምባሲ ጎን ሲሆን በተጨማሪም እኛን ለማግኘት ከፈለጉ የሚከተሉትን ይጠቀሙ
❤️https://t.me/sturaelclinic
❤️https://www.instagram.com/sturaelclinic
❤️https://www.sainturaelclinic.com
❤️9424
❤️+251-940464646 /0940565656 /0913349301 +251-116662556
/0116663741
❤️Rwanda St Just Beside Rwanda Embassy Addis Ababa Ethiopia.
❤️https://sturaelclinic@gmail.com

Telegram (https://t.me/sturaelclinic)
St. Urael Internal Medicine Clinic
ይህ የቅዱስ ኡራኤል የዉስጥ ደዌ ስፔሺያሊቲ ክሊኒክ ቻናል ነዉ።
አድራሻ፡- አዲስ አበባ፣ከ ቦሌ ወደ ቦሌ ሚካኤል በሚወስደዉ

Share with: