ሽንት መቆጣጠር አለምቻል
የሽንት አለመቆጣጠር ወይም የፊኛ ቁጥጥር ማጣት የተለመደ እና ብዙ ጊዜ ሊያሳፈር የሚችል ችግር ነው። የችግሩ ደረጃ በሚያስሉበት ወይም በሚያስነጥሱበት ጊዜ አልፎ አልፎ ከሚንጠባጠብ ወይም ከሚያመልጥዎ ሽንት አንስቶ እስከ ሽንት ለመሽናት ሲያስቡ መፀዳጃ ቤት እስኪደርሱ ድረስ ሽንትዎ በማጣደፍ ሽንት ቤት ከመድረስዎ በፊት ሽንት ማምለጥ ደረጃ ድረስ ሊደርስ ይችላል።
ምንም እንኳን ሰዎች በዕድሜ እየገፉ ሲሄዱ ብዙ ጊዜ የሚከሰት ቢሆንም የሽንት አለመቆጣጠር የእርጅና ጉዳይ በቻ ነዉ ብሎ መደምደም አይቻልም።
የሽንት አለመቆጣጠር በዕለት ተዕለት እንቅስቃሴዎ ላይ ተጽእኖ ካሳደረ የህክምና ባለሙያዎን ያማክሩ።
የሽንት መቆጣጠር ችግር አይነቶች
• በጫና ምክንያት የሚከሰት የሽንት መቆጣጠር ችግር (Stress incontinence) ፦ በማሳል፣ በማስነጠስ፣ በመሳቅ፣ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በማድረግ ወይም ከባድ ነገር በሚያነሱበት ወቅት ፊኛዎ ላይ ጫና ስለሚፈጠር የሽንት ማምለጥ ይከሰታል።
• ሽንት ሲያጣድፍዎ የሚከሰት የሽንት መቆጣጠች ችግር (Urge incontinence) ፦ በድንገት ሽንት አጣድፍዎ መፀዳጃ ቤት እስኪደርሱ ድረስ ሽንት የማምለጥ ችግር ሲሆን ይህ በኢንፌክሽን፣ በስኳርና በነርቭ ችግሮች ምክንያት ልከሰት ይችላል።
• ከመጠን በላይ ሞልቶ መፍሰስ፦ ይህ ሽንት ከሸኑ በኃላ ከፊኛዎ ሙሉ በሙሉ ወጥቶ ባዶ ሳይሆን ሲቀር ፊኛዎ ዉስጥ በመቅረቱ ምክንያት ተደጋጋሚ ወይም የማያቋርጥ የሽንት መንጠባጠብ ሲያጋጥም የሚከሰት ነዉ።
• ምንም የፊኛ ተግባር መስትጓጎል ሳይኖር የሚከሰት የሽንት መቆጣጠር አለመቻል፦ ይህ የአካል ወይም የአእምሮ እክል በጊዜ ወደ መጸዳጃ ቤት ሀሄድን በሚከለክልብተ ወቅት የሚከሰት ነዉ።
• ከአንድ በላይ( ድብልቅ) የሽንት መቆጣጠር ችግር መንስኤዎች ሲኖሩ፦ ከአንድ በላይ የሽንት መቆጣጠር ችግር መንስ ኤ ሲያጋጥም የሚከሰት ነዉ።
ለሽንት መቆጣጠር አለመቻል አጋላጭ ነገሮች
የሽንት አለመቆጣጠር አለመቻልን የመጋለጥ እድልን የሚጨምሩ ምክንያቶች የሚከተሉትን ያካትታሉ
1. ፆታ፦ ሴቶች ከወንዶች ይልቅ በጫና ምክንያት ለሚከሰት የሽንት አለመቆጣጠር ችግር የመጋላጥ እድላቸዉ ከፍተና ነዉ። ለዚህ ልዩነት እርግዝና፣ ልጅ መውለድ፣ ማረጥና ተፈጥሮያዊ የሴቶች የሰውነት አካል አቀማመጥ ለችግሩ ምክንያት ሊሆኑ ይችላል።ነገር ግን የፕሮስቴት ዕጢ እብጠት ያላቸዉ ወንዶችም ለችግሩ ተጋላጭ ናቸዉ።
2.እድሜ፦ እድሜ እየገፋ ሲሄድ በፊኛዎና በሽንትዎ መተላለፊያ ቱቦ ውስጥ ያሉት ጡንቻዎች በተወሰነ ደረጃ ጥንካሬያቸውን ያጣሉ። ከእድሜ ጋር የተያያዙ በሚከሰቱ ለውጦች ፊኛዎ የመያዝ አቅሙ ይቀንሳል። ይህም ያለእርስዎ ቁጥጥር የሽንት ማምለጥ ችግር እንዲከሰት ያደርጋል።
3.የክብደት ከመጣን በላይ መሆን፦ የሰዉነት ክብደት ከመተን በላይ መሆን በሽንት ፊኛዎ ላይ ጫና እንዲፈተር ያደርጋል፣ የህም የፊኛ ጡንቻዎች እንዲላሉ በማድረግ የሽንት ኣምምለጥ እንዲከሰት ሊያደርግ ይችላል።
4.ሲጋራ ማጨስ፦ ሲጋራ ማጨስ የሽንት ማምለጥ ችግር ተጋላችነት እንዲጨምር ያድረጋል
5.መሰል ችግር በቤተሰብ ዉስጥ መኖር፦ የቅርብ የቤተሰብ አባል የሽንት መቆራረጥ ችግር ካለበት በተለይም ሽንት ሲያጣድፍዎ የመቆጣጠር ችግር የመጋለጥ እድልዎ ከፍ ያለ ነው.
አድራሻችን፦ ቦሌ ሩዋንዳ ከሩዋንዳ ኤምባሲ ጎን ሲሆን በተጨማሪም እኛን ለማግኘት ከፈለጉ የሚከተሉትን ይጠቀሙ
https://t.me/sturaelclinic
https://www.instagram.com/sturaelclinic
https://www.sainturaelclinic.com
9424
+251-940464646 /0940565656 /0913349301 +251-116662556
/0116663741
Rwanda St Just Beside Rwanda Embassy Addis Ababa Ethiopia.
https://sturaelclinic@gmail.com22h
Telegram (https://t.me/sturaelclinic)
St. Urael Internal Medicine Clinic
ይህ የቅዱስ ኡራኤል የዉስጥ ደዌ ስፔሺያሊቲ ክሊኒክ ቻናል ነዉ።