094 046 4646/0940 565656    
info@sainturaelclinic.com
Follow Us:

View Blog

ክፍል ሁለት ለሽንት መቆጣጠር አለመቻል ምክንያቶች

ክፍል ሁለት
ለሽንት መቆጣጠር አለመቻል ምክንያቶች
ጊዜያዊ ምክንያቶች
አንዳንድ መጠጦች፣ ምግቦችና መድሃኒቶች ፊኛዎን በማነቃቃትና የሽንትዎን መጠን በመጨመር ሽንትን ሊያበዙ (እንደ ዳይሬቲክስ ሆነው ሊያገለግሉ) ይችላሉ። ከነዚህም ዉስጥ
❤️ የአልኮሆል መጠጥ
❤️ ካፊን
❤️ ካርቦኔትድ መጠጦች
❤️ አርቴፊሻል ማጣፈጫዎች
❤️ በቅመማ ቅመም፣ በስኳር ወይም በአሲድ የበለፀጉ ምግቦች በተለይም ፍራፍሬዎች
❤️ የልብና የደም ግፊት መድሃኒቶች፣ ማስታገሻዎችና የጡንቻ ለማላላት የሚሰጡ መዲሃኒቶች
❤️ ከፍተኛ መጠን ያለው ቫይታሚን ሲ

የሽንት አለመቆጣጠር በቀላሉ ሊታከም በሚችል የጤና ችግር ምክንያት ሊከሰት ይችላል፡-
❤️ የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን፦ ኢንፌክሽን ፊኛዎ እንዲቆጣ ያደርጋሉ፤ ይህም የመሽናት ከፍተኛ ፍላጎትና ማጣደፍ አንዳንዴም ሽንት የመቆጣጠር አቅምዎ እንዲቀንስ ያደርጋል።
❤️ የሰገራ ድርቀት፦ ደንዳኔ ከፊኛ አጠገብ እንደመገኘቱ መጠን ሁለቱንም በጋራ የሚያገለግሉ ነርቮች አሉ። ደረቅና የተጠራቀመ ሰገራ እነዚህ ነርቮች ከመጠን ባለፈ መልኩ እንዲነቃቁ ስለሚያደርግ ሽንት ቶሎ ቶሎ እንዲመጣ ያደርጋል።

ቀጣይነት ያለዉ የሽንት መቆጣጠ ችግር፦
የሽንት መቖጣጠር ችግር ዘላቂ ወይም ቀጣይነት ባለዉ ሁኔታ ሊከሰት የሚችል ሲሆን ይህም መሰረታዊ የሆኑ አካላዊ ለዉጦች ወይም ምክንያት ሊመጣ ይችላል።
 እርግዝና፦ የሆርሞን ለውጦችና የፅንሱ ክብደት መጨመር ጫና ስለሚፈጥር በጫና ምክንያት የሚከሰት የሽንት መቆጣጠር ችግር ያመጣል፡፡

 ወሊድ፦አምጦ መዉለድ ለፊኛ መቆጣጠሪያ የሚያስፈልጉት ጡንቻዎች እንዲላሉ እንዲሁም የፊኛ ነርቮችና ደጋፊ ህብረ ህዋሳት(ቲሹን) እንዲጎዳ በማድረግ የዳሌ ወለል ወደታች እንዲዠረገግ ያደርጋል። ይህም የሽንት ማምለት ጭግር ያመጣል።                                                                                 ከእድሜ ጋር የሚከሰት ለዉጥ፦ የፊኛ ጡንቻዎች ማርጀት የፍኛ ሽንት አጠራቅሞ የመያዝ አቅምን ይቀንሳል። እንዲሁም እድሜዎ እየገፋ ሲሄድ እርስዎ ሳይታወቅዎ የፊኛ መኮማተር እየበዛ ወይም እየጨመረ ይሄዳል።

 ማረጥ፦ሴቶች ካረጡ በኃላ የፊኛ እና የሽንት ቱቦን ሽፋን ጤናማ ለማድረግ የሚረዳ የኢስትሮጅ ሆርሞን መጠን ይቀንሳል። የእነዚህ ሕብረ ሕዋሳት መስራት መቀነስ አለመቻልን ሊያባብሰው ይችላል።

 የፕሮስቴት ማደግ፦ በተለይ እድሜያቸዉ በገፋ ወንዶች ላይ የሚከሰት ሲሆን ከፕሮስተት ዕጢ ማደግ ጋር በተያያዘ ችግሮች ሊከሰቱ ይችላሉ።

 ፐሮስቴት ካንሰር፦ የፕሮስቴት ካንሰር ኖሮ ህክምና ካላገኘ ወይም ለፕሮስተት ካንሰር የሚደረግ ህክምና በኃላ የሸንት ማምለት ችግር ሊከሰት ይችላል።
 የነርቭ ችግሮች፦ እንደ መልትፕል ስክሌሮሲስ፣ ፓርኪንሰን፣ ስትሮክ፣የጭንቅላት ዕጢ ወይም የህብለ ሰረሰር አደጋ መኖር ፊኛ ተገቢዉን ስራ እንዳይሰራ ሊያደርገዉ ስለሚችል ለሽንት ማምለት ጭግር ይዳርጋል።
 የሽንት መተላለፊያ መንገዶች ላይ የሚከሰት መዘጋት፦ ጠጠር፣ ዕጢዎችና ሌሎች ምግንያቶች የሽንት መተላለፊያ መንገዶችን በመዝጋት ለችግር ሊዳርጉን ይችላሉ።

አድራሻችን፦ ቦሌ ሩዋንዳ ከሩዋንዳ ኤምባሲ ጎን ሲሆን በተጨማሪም እኛን ለማግኘት ከፈለጉ የሚከተሉትን ይጠቀሙ
❤️https://t.me/sturaelclinic
❤️https://www.instagram.com/sturaelclinic
❤️https://www.sainturaelclinic.com
❤️9424
❤️+251-940464646 /0940565656 /0913349301 +251-116662556
/0116663741
❤️Rwanda St Just Be side Rwanda Embassy Addis Ababa Ethiopia.
❤️https://sturaelclinic@gmail.com22

Share with: