ቅሩንፉድና የጤና ጥቅሞቹ
ቅሩንፉድ ተፈጭቶና ሳይፈጭ እንዳለ ልንጠቀምበት የምንችለዉ የቅመም ዘር ነዉ። ሰዎች ብዙ ጊዜ ወደ ተለያዩ ምግቦችን ለማጣፈጥና ጣዕም ለመጨመር በቅመማ ቅመም ቅልቅል ውስጥ የተፈጨ ቅርንፉድ እንዲሁም ያልተፈጭ ቅርንፉድ ብቻዉን በምግብ አዘገጃጀት ውስጥ ይጨምራሉ።
ቅሩንፉድ (ክሎቭስ) ከፍተኛ የቤታ ካሮቲን ምንጭ ሲሆን ይህም የበለፀገ ቡናማ ቀለም እንዲሰጣቸው ይረዳቸዋል። የካሮቲን ቀለም( ፒግመንት) ጠቃሚ ፀረ-ባክቴሪያዎችና ፕሮቪታሚኖችን የያዘ ነዉ። ይህ ካሮቲን ፒግመንት የአይንን ጤንነት ወደሚጠብቀዉ ወደ ወደ ቫይታሚን ኤ ሊቀየር ይችላል።
1. ቁርንፉድ በሰዉነታችን ዉስጥ ቁጣን ለመቀነስ ይረዳል፦ ቅሩንፉድ ኢዩግኖል የሚባል ዉሁድ የያዘ ሲሆን ይህም በሰዉነታችን ዉስጥ ቁጣን( ኢንፍላሚሽንን) ለመቀነስ ይረዳል። ይህም በተለይ የመገጣጠሚያ ቁጣዎችን (አርትራይትስን) ለመቀነስ ይረዳል።
2. አንቲኦክሲዳንት ፀባይ አለዉ፦ ቅሩንፉድ በአንቲኦክሲዳንት የበለፀገ ነዉ። እነዚህ ውህዶች የሰውነት ሴሎችዎን የሚጎዱና ወደ በሽታ የሚወስዱትን ፍሪ ራዲካልስ ለመዋጋት ይረዳሉ። እነዚህን ፍሪ ራዲካልስ ከሰዉነታችን በማስወገድ የልብ፣የስኳርና የካንሰር ህመም ተጋላጭነታችንን ለመቀነስ ይረዳል።
3. ቁስለትን ለመቀነስ፦ ቅሩንፉድ የጨጓራ ቁስለትን ለመከላከል ይረዳል። ለቁስለት መፈጠር ዋነኛ ምክንያት የጨጓራ ንጣፍ መሳሳት ችግር ሲሆን ቁርንፉድ መሳሳቱን በመቀነስ እንዲወፍር ያደርጋል።
4. የጉበት የመስራት አቅምን ማዳበር፦ ቅሩንፉድ የጉበት የመስራት አቅምን ሊያሻሽሉ ይችላሉ።
5. ለምግብ ምንጭነት ያገለግላሉ፦ ቅሩንፉድ ማንጋኔዝ የሚባለዉን ማዕድን በብዛት የያዘ ነዉ። ማንጋኔዝ በሰዉነታችን ዉስጥ አጥንትን ለመጠገንና ሆርሞን ለመስራት የሚያገለግለዉን ኢንዛየም ለመስራት ያገለግላል። በተጨማሪም ማንጋኔዝ ጥሩ የቫይታሚን ኬ፣ የፖታሲየም፣ የቤታ ካሮቲንና ኢዩግኖል ምንጭ ነዉ።
ቅሩንፉድ ሲጠቀሙ ጥንቃቄ የሚሹ ነገሮች፦
❤️ ከመድሃኒት ጋር ግጭት መፈጠር፦ ቅሩንፉድ ዉስጥ ያለዉ ኢዩግኖል አንዳንዴ ከተወሰኑ መድሃኒቶች እንደ ዋርፋሪን ካሉ መድሃኒቶች ጋር አብሮ ሲወሰድ ግጭት ሊፈጥር ይችላል። ስለሆነም የደም ማቅጠኛ መድሃኒቶች እየወሰዱ ከሆነ የቅሩንፉድ ሻይም ይሁን ዘይት አብዝቶ ከመጠቀም ይቆጠቡ።
❤️ የስኳር ማነስ ( ሃይፖግላይሴሚያ)፦ ቅሩንፉድ የሰዉነት የስኳር መጠንን ሊቀንስ ይችላል። ስለሆነም የስኳር ህመም ካለዎ ቅሩንፉድን ከመጠን ባለፈ መጠን መዉሰድ ለስኳር መተን መቀነስ ሊዳርግ ስለሚችል በመጠኑ መጠቀም ይመከራል።
❤️ የአስፈላጊ ዘይት መርዛማነት ፦ የቅሩንፉድ አስፈላጊ ዘይት ዉስጥ ( essential oil) ያለዉ ኢዩጌኖል ወደዘይትነት ሳይቀየር ባለዉ ቅሩንፉድ ዉስጥ ካለዉ በጣም ይበልጣል። ንጹህ የክሎቭ ዘይትን መጠቀም መርዛማ ሊሆን ይችላል እና እንደ ማዞር አልፎ ተርፎም ኮማ ላሉ ምልክቶች ሊመራ ይችላል።
አድራሻችን፦ ቦሌ ሩዋንዳ ከሩዋንዳ ኤምባሲ ጎን ሲሆን በተጨማሪም እኛን ለማግኘት ከፈለጉ የሚከተሉትን ይጠቀሙ
❤️https://t.me/sturaelclinic
❤️https://www.instagram.com/sturaelclinic
❤️https://www.sainturaelclinic.com
❤️9424
❤️+251-940464646 /0940565656 /0913349301 +251-116662556
/0116663741
❤️Rwanda St Just Beside Rwanda Embassy Addis Ababa Ethiopia.
❤️https://sturaelclinic@gmail.com22