የትልቁ አንጀት ካንሰር
በትልቁ አንጀት ላይ የሚከሰት ካንሰር የትልቁ አንጀት ካንሰር በመባል ይታወቃል። ይህ ካንሰር በዋናነት በዕድሜ የገፉ ሰዎችን የሚያጠቃ ቢሆንም በየትኛዉም የዕድሜ ክልል ሊከሰት ግን ይችላል።
ካንሰሩ ከመከሰቱ በፊት
የህመም ምልክቶች
❤️ ከፊንጢጣ መድማት መከሰት ወይም ከሰገራ ጋር ደም መታየት
❤️ በመፀዳጃ አጠቃቀም ልማድዎ ላይ የማያቋርጥ ተከታታይነት ያለዉ ለውጥ መታየት፦ የሰገራ ይዘት ለውጥን ጨምሮ ተቅማጥ ወይም የሆድ ድርቀት መከሰት
❤️ እንደ ቁርጠት፣ ጋዝ መብዛት ያሉ የማያቋርጥ የሆድ ህመም መኖር
❤️ መፀዳጃ ቤት ከሄዱ በኃላ የሰገራ ሙሉ በሙሉ ያልወጣ ወይም የቀረ ስሜት መሰማት
❤️ የድካም ስሜት መኖር
❤️ የሰዉነት ክብደት መቀነስ ናቸዉ።
የአንጀት ካንሰር ያለባቸው ብዙ ሰዎች በበሽታው የመጀመሪያ ደረጃ ወቅት ላይ ምንም የህመም ምልክት አይታይባቸውም። የህመም ምልክቶች ሲከሰቱ፣ እንደ ካንሰሩ መጠንና በትልቁ አንጀትዎ ውስጥ እንደተከሰተበት ቦታ ላይ በመመስረት ሊለያዩ ይችላሉ።
የህመሙ መንስኤ
የህክምና ባለሙያዎች ለአብዛኛዎቹ የአንጀት ካንሰር መንስኤዎች ምን እንደሆነ እርግጠኛ አይደሉም።
ጠቅለል ተደርጎ ሲታይ የአንጀት ካንሰር የሚጀምረው በአንጀት ውስጥ ያሉ ጤናማ ሴሎች ዲ ኤን ኤያቸዉ ውስጥ ለውጦች (ሚውቴሽን) ሲፈጥሩ ነው። ጤናማ ሴሎች (ህዋሶች) በመከፋፈልና በማደግ ሰውነትዎ በመደበኛነት ስራዉን በአግባቡ እንዲወጣ ያደርጋሉ። ነገር ግን የአንድ ሴል ዲ ኤን ኤ ተጎድቶ ወደ ካንሰርነት ከተቀየረ ሰዉነታችን አዳዲስ ሴሎች ማምረት ባያስፈልገዉም ካንሰር ሴሎች መከፋፈላቸውን ይቀጥላሉ። እነዚ ሴሎች እየተጠራቀሙ ሲሄዱ ዕጢ ይፈጥራሉ። በሂደት ወይም ከጊዜ በኋላ የካንሰር ሕዋሳት ማደግ በአቅራቢያ ያሉ መደበኛ ሕብረ ሕዋሳትን እያጠፉ ይመጣሉ። ከዚህም አልፎ የካንሰር ሕዋሳት ወደ ሌሎች የሰውነት ክፍሎች በመሄድና በመሰራጨት (metastasis) እዚያው ክምችት ሊፈጥሩ ይችላሉ።
አድራሻችን፦ ቦሌ ሩዋንዳ ከሩዋንዳ ኤምባሲ ጎን ሲሆን በተጨማሪም እኛን ለማግኘት ከፈለጉ የሚከተሉትን ይጠቀሙ
❤️https://t.me/sturaelclinic
❤️https://www.instagram.com/sturaelclinic
❤️https://www.sainturaelclinic.com
❤️9424
❤️+251-940464646 /0940565656 /0913349301 +251-116662556
/0116663741
❤️Rwanda St Just Beside Rwanda Embassy Addis Ababa Ethiopia.
❤️https:/
Telegram (https://t.me/sturaelclinic)
St. Urael Internal Medicine Clinic
ይህ የቅዱስ ኡራኤል የዉስጥ ደዌ ስፔሺያሊቲ ክሊኒክ ቻናል ነዉ።