የአንጀት መነጫነጭ
(Irritable bowel syndrome (IBS))
የአንጀት መነጫነጭ ጨጓራንና አንጀትን የሚያጠቃ ሊጎድ የሚችል የተለመደ የጤና ችግር ነዉ። የአንጀት መነጫነጭ ለረጅም ጊዜ መታከም የሚያስፈልግዎ ሥር የሰደደ በሽታ ነው።
የአንጀት መነጫነጭ ችግር ያለባቸው ጥቂት ሰዎች ብቻ ከባድ የህመም ምልክቶች ሊያሳዩ ይችላሉ። አንዳንድ ሰዎች አመጋገብን፣ የአኗኗር ዘይቤንና ጭንቀትን በመቆጣጠር ምልክቶቻቸውን መቆጣጠር ይችላሉ። በጣም ከባድ የሆኑ የህመም ምልክቶች ያለባቸዉ ሰዎች በመድሃኒት እና በምክር ሊታከሙ ይችላሉ።
የአንጀት መነጫነጭ የአንጀት ቲሹዎች ላይ ለውጦችን አያመጣም ወይም የአንጀት ካንሰር (የኮሎሬክታል ካንሰር) ተገላጭነት አደጋን አይጨምርም።
የህመም ምልክቶች
የአንጀት መነጫነጭ የህመም ምልክቶች የተላያዩ ሲሆኑ ለረጅም ጊዜ የዘለቁ ናቸዉ። በጣም ከተለመዱ የህመም ምልክቶች ዉስጥ
· የሆድ ህመም ወይም የሆድ ቁርጠት
· የሆድ መነፋት
· መፀዳጃ ቤት የሚሄዱበት ልማድ መቀየር
· መፀዳጃ ቤት ሲቀመጡ አየር መብዛት
· መፀዳጃ ቤት ከተጠቀሙ በኃላ ያልጨረሱ ስሜት መኖር ወይም መከሰት
የህክምና በለሙያዎን ማማከር የሚገባዎ መቼ ነዉ?
ከአንጀትዎ ወይም ከመፀዳጃ አጠቃቀምዎ ጋር የተገናኙ ለዉጦች በዘላቂነት ከተከሰቱና ከአንጀት መነጫነጭ የህመም ምልክቶች ዉጪ ሌሎች ተጨማሪ ምልክቶች ካለዎ የህክምና ባለሙያዎን ያማክሩ። የሚከተሉት የህመም ምልክቶች ካለዎ የህክምና ባለሙያዎ ማማከርዎን አይዘንጉ
~ የክብደት መቀነስ
~ ማታ ማታ ተቅማጥ መኖር
~ ከፊንጢጣ መድማት ካለዎ
~ ከብረት ማዕድን ጋር የተያያዘ የደም ማነስ ካለዎ
~ ምክንያቱ ያልታወቀ ማስታወክ
~ ሰገራ በመቀመጥ ወይም ጋዝ ሲያስወጡየሆድ ህመምዎ የማይቀንስ ከሆነ የህክምና ባልሙያዎን ያማክሩ።
አድራሻችን፦ ቦሌ ሩዋንዳ ከሩዋንዳ ኤምባሲ ጎን ሲሆን በተጨማሪም እኛን ለማግኘት ከፈለጉ የሚከተሉትን ይጠቀሙ
❤️https://t.me/sturaelclinic
❤️https://www.instagram.com/sturaelclinic
❤️https://www.sainturaelclinic.com
❤️9424
❤️+251-940464646 /0940565656 /0913349301 +251-116662556
/0116663741
❤️Rwanda St Just Beside Rwanda Embassy Addis Ababa Ethiopia.
❤️https:/