እድሜ፦ አንድ ሰዉ እድሜዉ እየጨመረ ሲመጣ ቫይታሚን ቢ 12 ከአንጀቱ የመመጠጥ አቅም እየቀነሰ ይመጣል።
ቀዶ ጥገና፦ ክብደት ለምቀነስ ተብሎ አንጀትና ጨጓራ ላይ የሚደረግ ቀዶጥገና

መጠጥ፦ መጠጥ( አልኮሆል) አብዝተዉ የሚጠጡ ሰዎች ወይም ከመጠን ባለፈ መጠን መጠጣት ንጥረነገሮች በአግባቡ ከአንጀታችን እንዳይመጠጡ ያደርጋል ፤ በተጨማሪም በቂ ካሎሪ( ሃይል) እንዳንመገብ ያደርጋል። በቂ ቫይታሚን ቢ 12 በሰዉነትዎ ዉስጥ እንደሌለ ማሳያዎ የምላስ ማባጥና መቆጣት ነዉ።

አትሮፊክ ጋስትራይትስ፦ ይህ የጨጓራ የዉስጠኛዉ ሽፋን ሲቀጥን የሚከሰት ነዉ

ፐርኒሽየስ አኒሚያ( የደም ማነስ)፦ ይህ አይነት የደም ማነስ ሲከሰት ቫይታሚን ቢ 12 የመመጠጥ አቅም ይቀንሳል።

ትንሹ አንጀትን የሚጎዱ ህመሞች መኖር፦ ለምሳሌ ክሮንስ ዲዚዝ፣ ሲሊያክ ዲዚዝ፣የባክቴሪያና ፓራሳይት ኢንፌክሽን መኖር

የበሽታ መከላከል አቅምን የሚጎዱ ችግሮች ለምሳሌ ግሪቭስ ዲዚዝና ሉፐስ ያሉ

መድሃኒቶች፦ ቫይታሚን ቢ12 የመመጠጥ አቅምን የሚቀንሱ መድሃኒቶች ያሉ ሲሆን ለምሳሌ የጨጓራ መድሃመድሃኒቶች ( ኦሜፕራዞል፣ ፓንቶፕራዞል፣ ኢሶሜፔራዞልና ላንሶፕ፣ ፋሞቲዲን)፣ እንደሜትፎርሚን ያሉ የስኳር መድሃኒቶች

ቬጅቴሪያን( አትክልት ብቻ) የሚመገቡ ከሆነ፦እንደ ስጋ፣ወተት አይብና እንቁላል ያሉ የእንስሳት ተዋፅኦ የሆኑ ምግቦችን የማይመገቡ ከሆነ ለቫይታሚ ቢ 12 እጥረት የመጋለጥ እድልዎ ከፍተኛ ነዉ።
የቫይታሚን ቢ 12 እጥረት የህመም ምልክቶች

የደም ማነስ

ድካም፣ የራስ ምታት

የልብ ምት መፍጠን ወይም ትንፋሽ ማጠር

የቆዳ መገርጣት

የምላስ መላጣ መሆን

የሆድ ድርቀት፣ ተቅማጥ፣የምግብ ፍላጎት መቀነስ ወይም ጋዝ ማብዛት

የነርቭ ላይ ችግሮች፦ መደንዘዝ ወይም መጠቅጠቅ፣ የጡንቻ መስነፍ ፣ ሲራመዱ መቸገር

የአይን እይታ መጋረድ

የአዕምሮ ችግሮች፦ ድብታ፣ የማስታወስ ኣቅም መቀነስ፣ የባህሪ ለዉጦችና የመሳሰሉት ናቸዉ።
መከላከል
1. የእንስሳት ተዋፅኦ የሆኑ ምግቦችን በአግባቡ መመገብ
2. የአንስሳት ትዋፅኦዎችን በህመም ምክንያትመ ይሁን በሌላ ምክንያት የማይመገቡ ከሆነ በቫይታሚን ቢ 12 የበለፀጉ ምግቦችን አሊያም ሰፕሊመንቶችን ይጠቀሙ
3. ለቫይታሚን ቢ 12 እጥረት ምክንያቱ ህመሞች ከሆኑ አሊያም የሚወስዱት መድሃኒት ከሆነ የህክምና ባለሙያዎን ያማክሩ
Share with: