አንግዲያዉስ የሚከተሉተሉትን ምግቦች ከመመገብ ይቆጠቡ
የጉበት ስብ መሆን የሚመጣዉ ጉበትዎ ዉስጥ ከመጠን ያለፈ ስብ ሲጠራቀም የሚመጣ ነዉ። ይህ ችግር በአግባቡ ካልታከመ ስር ለሰደደ የጉበት ህመም ( ሲርሆሲስ ) ከነዳረጉም በላይ ለጉበት መድከምና መስራት ማቆም ችግር ይዳርጋል።
የጉበት ስብ መሆን ችግር ሲኖር መመገብ የሌለብዎ
የጉበት
ስብ መሆን ችግር ካለዎ የህክምና ባለሙያዎ የተውሰኑ የምግብ አይነቶችን እንዳይመገቡ ሊከለክልዎ ወይም እንዲቀንሱ ልመክርዎ ይችላል። እነዚህ ምግቦች የሰዉነት ክብደትዎንና የደም የስኳር መጠን እንዲጨምር ሊያደርጉ ይችላሉ።
1. አልኮሆል፦ አልኮሆል ለጉበት ስብ መሆን ችግርና ለሌሎች የጉበት ችግሮች ዋነኛ መንስኤ ነዉ።
2. ስኳር የተጨመረባቸዉ ምግቦች፦ እንደ ከረሜላ፣ ኩኪሶች፣ የሶዳ ( ለስላሳ መጠጦች)ና የፍራፍሬ ጭማቂዎች ካሉ ጣፋጭ ምግቦች ይራቁ። ከፍተኛ የደም የስኳር መጠን ካለዎ በጉበት ውስጥ የስብ ክምችት መጠን እንዲጨምር ያደርጋል።
3. የተጠበሱ ምግቦች፦ የተጠበሱ ምግቦች ከፍተኛ የሆነ የስብና ካሎሪ መጠን አለቸዉ።
4. ጨዉ የበዛበት ምግቦች፦ በጣም ብዙ ጨው መጠቀም የጉበት ስብ መሆን አደጋን ይጨምራል
5. ነጭ ዳቦ፣ ሩዝና ፓስታ፦ በተለምዶ ነጭ ዱቄት የሚባለዉ በከፍተኛ ሁኔታ በፋብሪካ ተቀነባብሮ የሚዘጋጅ ሲሆን ከዚህ ዱቄት የሚዘጋጁ የምግብ አይነቶች በቂ ፋይበር ስለማይኖረዉ ከጥራጥሬዎች የበለጠ የደምዎን ስኳር መጠን ከፍ እንዲል ሊያደርጉ ይችላሉ።
6. ቀይ ስጋ፦ የበሬ ስጋ ጤናማ ያልሆነ የስብ አይነቶችን በከፍተኛ መጠን ይይዛል።
Share with: