የማህፀን በር ካንሰር የሚመጣዉ በሂዩማን ፓፒሎማ ቫይረስ (HPV) ኢንፌክሽን አማካይነት ነዉ። ኢንፈክሽኑ የሚተላለፈዉ በግብረስጋ ግንኙነት አማካይነት ነዉ። ምንም እንኳ አብዛኛዉን ጊዜ የሰዉነት በሽታ መከላከል አቅም ኢንፌክሽኑን ከሰዉነት የሚያሶጣ ቢሆንም ከፍተኛ ተጋላጭነት ባላቸዉና የማይቋረጥ ወይም ቀጣይነት ያለዉ የኤችፒቪ ኢንፌክሽን ያልተለመዱ ሴሎች እንዲፈጠሩ ሊያደርግ ይችላል፤ ይህም በሂደት ወደ ካንሰርነት ይቀየራል።
የማኅፀን አንገት ወይም ጫፍ ለረጅም ጊዜ የቆየ ወይም የማያቋርጥ የኤች ፒቪ (HPV) ኢንፌክሽን ካልታከመ በ95%ዎቹ ላይ የማህፀን በር ካንሰርን ያስከትላል።
ያልተለመዱ ህዋሶችና ሴሎች በማህፀን በር ጫፍ ላይ ከተፈጠሩ በኃላ ወደ ካንሰርነት ለመሸጋገር ከ15-20 አመት ይፈጃል ወይም ይወስዳል። ነገርግን የሽታ የመከላከል አቅማቸው በተዳከመ ሴቶች ላይ ለምሳሌ እንደ ኤች አይ ቪ( HIV) ያለ ህመም ኖሮዋቸዉ ህክምና ካላገኙ ይህ ሂደት ፈጣንና ከ5-10 አመት ብቻ ሊወስድ ይችላል።
ለካንሰር እድገት ከሚያጋልጡ ምክንያቶች መካከል

የኤችፒቪ (HPV) አይነት ኦንኮጄኔሲቲ ደረጃ

የበሽታ መከላከል ደረጃ ወይም ሁኔታ

ሌሎች በግብረ ሥጋ ግንኙነት የሚተላለፉ ኢንፌክሽኖች መኖር

የወሊድ ብዛት

የመጀመሪያ እርግዝና ያረገዙበት ወቅት በወጣትነት ወይም ለጋነት እድሚ ክልል ከነበረ

ሆርሞንነት ያለዉ የወሊድ መከላከያ የሚጠቀሙና

ሲጋራ ማጨስ ይጠቀሳሉ።
Share with:
መንስኤ