ብዙ ሰዎች ብረት ነክ ነገሮችን ሲነኩ አሊያም ሰዎችን ሲጨብጡ በድንገት የመንዘር ባህሪ ይሰማቸዋል።
ይህ
ሁነት ስታቲክ ኤሌክትሪክሲቲ ይባላል።
እንደሚታወቀዉ ሁሉም ነገር የተሰራዉ ወይም የተገነባዉ አተም( Atom) ከሚባሉ ጥቃቅን ነገሮች ነዉ።
አተም በኒውክለሱ ዉስጥ ፕሮቶንስ የሚባሉ ፖዘቲቭ ቻርጅ ያላቸዉ ቅንጣቶች የያዘ ሲሆን በዙሪያዉ ደግም ኔጋቲቭ ቻርጅ ባላቸዉ ኤሌክትሮንስ በሚባሉ ቅንጣቶች የተከበበ ነዉ።
በአንድ አተም ዉስጥ ያሉ ኤሌክትሮንስና ፕሮቶንስ ቁጥር እኩል ከሆነ ቻርጁ ኒዉትራል ይሆናል።
ነገር ግን ሁለት አቶሞች ከተፋተጉ ከሁለት አንዳቸዉ ኔጋቲቭ ቻርጅ ሊያገኙ ወይም ሊያጡ ይችላሉ።
ይህ የተፈጠረዉ የቻርጅ ያለመመጣጣን ስታቲክ ኤሌክትሪክሲቲ ይፈጥራል።
ሰዎች ብረት ነክ ነገር ሲነኩ በድንገት የኤሌክትሪክ ንዝረት (ሾክ) የሚሰማቸዉ ከመጠን ያለፈ ኤሌክትሪካል ቻርጅ ኤሌክትሪክ በደንብ በማይሰራጭባቸው ቁሳቁሶች ውስጥ በሚጠራቀምበት ወቅት ነዉ። ስለሆነም ይህ ሰዉ ፖዘቲቭ ቻርጅ ያለዉ ማንናዉንም ነገር ሲነካ ኤሌክትሮኖች ከሱ ወደ ዕቃዉ በፍጥ ነት ስለሚፈሱ አስደንጋጭ የሆነ ንዝረት እንዲከሰት ያደርጋል።
ስለሆነም ሰዎችን ወይም ብረት ነክ ነገሮችን ስንነካ የሚነዝረን ነገር የሆነ የህመም ችግር ስላለን ሳይሆን የኤሌክትሪካ ቻርጅ ልዩነቱን ለማስተካከል ኤሌክትሮኖች ከእርስዎ ወደ ፖዘቲቭ ቻርጅ ወዳለዉ ነገር ፍሰት በሚያደርጉበት ወቅት የሚከሰት ነዉ።
ስለሆነም መሰል ችግር ያለበት ሰዉ ችግሩ የህመም ምልክት መስሎት ስጋት ዉስጥ መግባት የለበትም ማለት ነዉ።
Share with: