ከመጠን ያለፈ ከአንገት በላይ ማላብ በተለያዩ ምክንያቶች የሚከሰት ሲሆን ከነዚህ ምክያቶች ዉስጥ አንዱ የቫይታሚን ዲ እጥረት ነዉ።
የጭንቅላት ላብ ብቻውን የቫይታሚን ዲ እጥረት ምልክት አይደለም፣ነገር ግን ከሌሎች መሰረታዊ ጉዳዮች ጋርም ሊዛመድ ይችላል።
የጭንቅላት ወይም ከአንገት በላይ ላብ ክራኒዮፋሺያል ሃይፐርሃይድሮሲስ የሚባል ሲሆን ይህም የራስ ቅል ቆዳ፣ ግንባርና ፊት ላይ ላቦቱ ይከሰታል። ላብ የሰውነትን ሙቀት ለመቆጣጠር የሚረዳ ተፈጥሯዊ የሰውነት ምላሽ ነው፤ ነገር ግን በተወሰኑ የሰዉነት ቦታዎች ላይ ከመጠን በላይ ማላብ አስጨናቂና በሰውነት ውስጥ ያለውን የሙቀት መቆጣጠሪያ ስርዓት አለመመጣጠን ሊያመለክት ይችላል::
ከቫይታሚን ዲ ዉጪ ከመጠን ያለፈ የጭንቅላት ላብ ሊያመጡ የሚችሉ
1. የሆርሞን መለዋወጥ፦ በተለይ ሲቶች ላይ የወር አበባ ሲቋረጥ
2. ጭንቀት
3. ሙቀትና ወበቅ
4. የተወሰኑ የህመም አይነቶች፦ ስኳር፣ የታይሮይድ ሆርሞን መብዛትና የተወሰንይ ኢንፌክሽኖች
5. የላብ ዕጢዎች ከመጠን በላይ መስራት ናቸዉ።
ስለሆነም ከመጠን ያለፈ የጭንቅላት ላብ ካለዎ የቫይታሚን ዲ እጥረት ምልክት ሊሆን ስለሚችል ወደ ህክምና ተቋም በመሄድ የቫይታሚን ዲ መጠንዎን ይለኩ።
Share with: