የቆዳ ድርቀት(Skin dryness)
ክፍል አንድ
የቆዳ ድርቀት መኖር ቆዳን ሸካራማ፣ የማሳከክ፣ የመላላጥ ወይም የመቀረፍ አይነት ስሜት እንዲሰማው ያደርጋል።
የቆዳ ድርቀት በየትኛዉም የዕድሜ ክልል ያሉ ሰዎችን የሚያጠቃ ሲሆን የሚከሰትበት የቆዳ ክፍል ከሰዉ ሰዉ ይለያያል።
የቆዳ ድርቀት ወይም ዜሮሲስ ወይም ዜሮደርማ ብዙ መንስኤዎች ያሉት ሲሆን ከነዚህም ዉስጥ ቀዝቃዛ አሊያም ደረቅ የአየር ፀባይ ፣ የፀሃይ ቃጠሎ፣ ደረቅ ሳሙናዎችና ከልክ ያለፈ መታጠብ ዋና ዋናዎቹ ምክንያቶች ናቸዉ።
የህመም ምልክቶች
የቆዳ ድርቀት ብዙዉን ጊዜ ጊዜያዊና ወቅታዊ ሊሆን ይችላል አሊያም ለረጅም ጊዜ ህክምና ሊፈልግ ይችላል። የቆዳ ድርቀት የህመም ምልክቶች እንደ እድሜዎ፣ የጤና ሁኔታ፣የሚኖሩባት አካባቢ ኣንድ ፀሃይ ተጋልጦ ሊለያይ ይችላል።
❤ የሻከረ ቆዳ ስሜት
❤ የቆዳ ማሳከክ
❤ ከመጠነኛ እስከ ከፍተና ደረጃ ያያዘ የቆዳ መላላጥ ወይም ቅርፊት መያዝ
❤ የቆዳ መሰነጣጠቅ
❤ እንደ "ደረቅ ወንዝ" የተሰነጠቀ ቆዳ በተለይ እግር ላይ
❤ ትናንሽ መስመሮች ወይም ስንጥቆች
❤ በነጭ ቆዳ ላይ ቅላት ወይም በጥቁር ቆዳ ላይ ግሬይ ቀለም መታየት ካለ
❤ ቆዳዎ ላይ የመወጣጠር ስሜት መኖር ናቸዉ።
አድራሻችን፦ ቦሌ ሩዋንዳ ከሩዋንዳ ኤምባሲ ጎን ሲሆን በተጨማሪም እኛን ለማግኘት ከፈለጉ የሚከተሉትን ይጠቀሙ
❤️https://t.me/sturaelclinic
❤️https://www.instagram.com/sturaelclinic
❤️https://www.sainturaelclinic.com
❤️9424
❤️+251-940464646 /0940565656 /0913349301 +251-116662556
/0116663741
❤️Rwanda St Just Beside Rwanda Embassy Addis Ababa Ethiopia.
❤https://sturaelclinic@gmail.com