የእግር ጉዞ/ አርምጃና የጤና ጥቅሙ(walking and health benefits tips)
የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ሲባል የግድ ዉስብስብ ያለ መሆን የለበትም።
ይልቁንስ በየእለቱ ቀለል ያለ እንደ ፈጣን የእግር ጉዞ ማድረግ ጤናማ ህይወት እንዲኖርዎ ያግዛል።
ስለሆነም በመደበኛነት የእግር ጉዞ ማድረግ ወይም ወክ ማድረግ· ጤናማ የሰዉነት ክብደት እንዲኖርዎ እንዲሁም የሰዉነት ስብ መጠንን ለመቀነስ ይረዳል·
❤️ እንደ የልብ ህመም፣ ስትሮክ፣ የደም ግፊት ካንሰርንና የስኳር ህመምን ጨምሮ ብዙ የጤና ችግሮችን ለመከላከልና ለማከም ይረዳል
❤️ የልብና የደም ዝዉዉር ስርዓትን ብቃት ለማሻሻል ይረዳል·
❤️ አጥንትንና ጡንቻዎችን ለማጠንከር ይረዳል·
❤️ የሰዉነት ጡንቻዎች አደጋን መቋቋምና ጽኑ እንዲሆኑ ( ኢንዱራንስ) ያደርጋል።·
❤️ የሰዉነት ኃይል/ብርታት እንዲጨምር ያደርጋል·
❤️ ስሜትዎን፣ ግንዛቤዎን፣ የማስታወስ ችሎታዎንና እንቅልፍዎን ያሻሽላል።·
❤️ የሰዉነትዎን ሚዛንና ቅንጅት ያሻሽላል።·
❤️ የሰዉነት በሽታ የመከላከል አቅም ያሻሽላል
❤️ ጭንቀትንና ውጥረትን ይቀንሳል።
በፍጥነት ራቅ ያለ ቦታ በተደጋጋሚ በተጓዙ ቁጥር የሚያገኙት የጤና ጥቅሞቹ የበለጠ ይሆናል።
አድራሻችን፦ ቦሌ ሩዋንዳ ከሩዋንዳ ኤምባሲ ጎን ሲሆን በተጨማሪም እኛን ለማግኘት ከፈለጉ የሚከተሉትን ይጠቀሙ
❤️https://t.me/sturaelclinic
❤️https://www.instagram.com/sturaelclinic
❤️https://www.sainturaelclinic.com
❤️9424
❤️+251-940464646 /0940565656 /0913349301 +251-116662556
/0116663741
❤️Rwanda St Just Beside Rwanda Embassy Addis Ababa Ethiopia.
❤️https://sturaelclinic@gmail.com