094 046 4646/0940 565656    
info@sainturaelclinic.com
Follow Us:

View Blog

ራኒቲዲን (Ranitidine)


ራኒቲዲን (Ranitidine) የሚባለዉ መድሃኒት እንዳይታዘዝ ታገደ
ራኒቲዲን የጨጓራ መድሃኒት ሲሆን የጨጓራን አሲድ የማመንጨት አቅም እንዲቀንስ የሚያደርግ ነዉ።
ይህ መድሃኒት የጨጓራና ትንሹ አንጀት ቁስለትንና ከመጠን ያለፈ የጨጓራ አሲድን ለመቀነስና ለማከም እንዲሁም የቃርና የምግብ መተላለፊያ ቱቦ ( ኢሶፋገስ) በአሲድ ምክንያት መቃጠልን ለመቀነስ ይረዳል።
ይሁንና ጥናቶች እንዳሳዩት ራኒቲዲን ካንሰር ሊያመጣ የሚችል ንጥረ ነገር ( ካርሲኖጂንስ) በዉስጡ ስለተገኘበት ለህሙማን እንዳይታዘዝ ታግዷል።
በራኒቲዲን ዉስጥ የተገኘዉና ሰዎች ላይ ካንሰር ሊያመጣ ይችላል የተባለዉ ንጥረ ነገር ኤንዴኤምኤ-NDMA( ኤን- ናይትሮሶድሜቲላማይን) የሚባል ነዉ።
መድሃኒቱ ከመደበኛው የአካባቢ ሙቀት መጠን በላይ ከፍ ባለ ክፍል ዉስጥ የሚከማች ከሆነ የኤንዲኤምኤ ንጥረ ነገር መጠን በመዲሃኒቱ ዉስጥ እንዲጨምር ያደርጋል።
እንዲሁም በአማካይ የክፍል ሙቀት መጠን ዉስጥ ቢከማችም በሂደት የንጥረ ነገሩ መጠን በጊዜ ሂደት እየጨመረ ይሄዳል።
ይህም ሰዎችን ተቀባይነት ለሌላቸው የኤንዲኤምኤ (NDMA) መጠን እንዲጋለጡ ያደርጋቸዋል።

ራኒቲዲን ከተለያዩ የአንጀት የካንሰር አይነቶች ጋር ግንኙነት ሊኖረው ይችላል። ከነዚህም ዉስጥ፦
❤️     የትልቁ አንጀት ( ኮሎሬክታል )
❤️     የጨጓራ
❤️     የጉበት
❤️     የቆሽት
❤️     የምግብ መተላለፊያ ቱቦና
❤️     የጉሮሮና ካንሰሮች ናቸዉ።

አድራሻችን፦ ቦሌ ሩዋንዳ ከሩዋንዳ ኤምባሲ ጎን ሲሆን በተጨማሪም እኛን ለማግኘት ከፈለጉ የሚከተሉትን ይጠቀሙ
❤️https://t.me/sturaelclinic
❤️https://www.instagram.com/sturaelclinic
❤️https://www.sainturaelclinic.com
❤️9424
❤️+251-940464646 /0940565656 /0913349301 +251-116662556
/0116663741
❤️Rwanda St Just Beside Rwanda Embassy Addis Ababa Ethiopia.
❤️https://sturaelclinic@gmail.com

Share with: