ካልሲያም(Calcium)
ካልሲየም ሰዉነታችን ጠንካራ አጥንትና የተለያዩ በጣም አስፈላጊ ስራዎችን ሰዉነታችን እንዲያከናዉን የሚረዳ መዕድን ነዉ። በሰዉነታችን ዉስጥ በብዛት ከሚገኙ ማዕድናት ዉስጥ ካልሲየም ዋነኛዉ ነዉ።
በሰውነት ውስጥ ያሉዉ ሁሉም ካልሲየም ማለት ይቻላል (99%) በአጥንትና በጥርስ ውስጥ ይከማቻል። ይህም ለጥርስና አጥንት መዋቅርና ጥንካሬ ይሰጣቸዋል።
ካልሲየም የሰውነታችን ጡንቻዎች እንዲንቀሳቀሱና ነርቮች መልዕክቶችን ከአንጎል ወደ እያንዳንዱ የሰውነታችን ክፍሎች እንዲያስተላልፉ የሚያደርግ ወይም የሚያግዝና የልብና የደም ቧንቧ ስራቸዉን እንዲያከናዉኑ ያደርጋል።
ካልሲየም የደም ሥሮች ደምን በሰውነታችን ውስጥ እንዲያንቀሳቅሱ ይረዳል ፤ እንዲሁም ብዙ አገልግሎት ወይም ተግባራትን ሊሰጡ የሚችሉ ሆርሞኖች እንዲለቀቁ ያደርጋል።
ከካልሲየም ጎን ለጎን ሰዎች ቫይታሚን ዲ ያስፈልጋቸዋል፤ ምክንያቱም ቫይታሚን ዲ ሰውነታችን ካልሲየም ከአንጀት ወደ ሰዉነታችን እንዲመጠጥ ያደርጋልና።
ካልሲየም ለምን ጉዳይ እንፈልገዋለን?
1. ለአጥንት ጤንነት፦ የሰዉነታችን 99% ካልሲየም የሚገኘዉ በአጥንትና ጥርስ ዉስጥ ነዉ። ካልሲየም ለአጥንት እድገት፣ መጎልበትና ጥገና አስፈላጊ መዐድን ነዉ። ህፃናት ላይ ካልሲየም ለአጥንት እድገት በታም አስፈላጊ ነገር ነዉ። አንድ ሰዉ ማደግ ሲያቆም ካልሲየም አጥንትን ለመጠበቅ እንዲሁም የአጥንት መሳሳትን ለከላከል ይረዳል። አንዲት እናት ስታርጥ ( የወር አበባዋ ሲቋረጥ) ከወንዶች ይልክ በከፍተኛ ሁኔታ የአጥንት መሳሳት ችግር ይገጥማታል። ስለሆነም ሀኪሞች የካልሲየም ሰፕሊመንት እንዲወስዱ ይመክራሉ.
2. ለጡንቻ መኮማተር (contraction):- ካልሲየም የጡንቻ መኮማተርን ለመቆጣጠር ይረዳል። ነርቭ ጡንቻን ሲያነቃቃ ሰውነት ካልሲየም እንዲለቀቅ ያደርጋል። ካልሲየም በጡንቻዎች ውስጥ ያሉ ፕሮቲኖች የመኮማተር ሥራን እንዲያከናዉኑ ያግዛል። ሰውነት ካልሲየምን ከጡንቻ ውስጥ ሲያስወጣ ጡንቻው ዘና ይላሉ ወይም ይፍታታሉ።
3. ለልብና ደም ቧንቧ ስርዓት፦ ደም እንዲረጋ ያግዛል፣ የልብ ጡንቻዎች በአግባቡ እንዲሰሩ ያደርጋል። ካልሲየም በደም ሥሮች ዙሪያ ያለውን ለስላሳ ጡንቻ ዘና እንዲል (relaxes the smooth muscle ) ያደርጋል።
4. ሌሎች አገልግሎቶች፦ ካልሲየም ለብዙ ኢንዛይሞች ተባባሪ አካል (co-factor ) ነው። ክልሲየም ከሌለ አንዳንድ በታም ቁልፍ የሆኑ ኢንዛየሞች ስራቸዉን በአግባቡ መከወን አይችሉም።
አድራሻችን፦ ቦሌ ሩዋንዳ ከሩዋንዳ ኤምባሲ ጎን ሲሆን በተጨማሪም እኛን ለማግኘት ከፈለጉ የሚከተሉትን ይጠቀሙ
❤️https://t.me/sturaelclinic
❤️https://www.instagram.com/sturaelclinic
❤️https://www.sainturaelclinic.com
❤️9424
❤️+251-940464646 /0940565656 /0913349301 +251-116662556
/0116663741
❤️Rwanda St Just Beside Rwanda Embassy Addis Ababa Ethiopia.
❤️https://sturaelclinic@gmail.com