094 046 4646/0940 565656    
info@sainturaelclinic.com
Follow Us:

View Blog

የጡት ማቆጣትና ኢንፌክሽን ( ማስታይትስ) ✍️ክፍል አንድ


የጡት ማቆጣትና ኢንፌክሽን ( ማስታይትስ)
✍️ክፍል አንድ

ማስታይትስ የጡት ህብረ ህዋስ መቆጣት ሲሆን አንዳንዴ የጡት ኢንፌክሽንንም ያጠቃልላል። ይህም የጡት ህመም፣ እብጠት፣ መቅላትና መሞቅ ( ተኩሳት) እንዲሰማዎ ያደርጋል።
ማስታይትስ አብዛኛዉን ጊዜ ጡት የሚያጠቡ እናቶችን የሚያጠቃ ሲሆን አንዳንዴ ግን ጡት በማያጠቡና ወንዶች ላይ ይከሰታል።
የጡት መቆጣትና ኢንፌክሽን ጡት የሚያጠቡ እናቶች ላይ መከሰት ድካምንንና የወለዱትን ልጅ መንከባከብ ሊቸገሩ ይችላሉ።

የህመም ምልክት
የህመም ምልክቶቹ በድንገት ሊጀምሩ ይችላሉ። እነርሱም
❤️ የጡት ላይ ህመም
❤️ ጡት ሲነካ ሙቀት መኖር
❤️ የጡት እብጠት
❤️ ጡት ሲነካ የጠጠረ ነገር መኖር
❤️ ጡት በሚያጠቡበት ወቅት የህመም ወይም የማቃጠል ስሜት ሞኖር
❤️ የጡት ቆዳ መቅላት
❤️ በአጠቃላይ የህመም ስሜት መኖር
❤️ የሰዉነት ትኩሳትና የመሳሰሉት ናቸዉ።

የህመም ምክንያቶች
ዋናው የማስታቲስ ህመም መንስኤ በጡት ውስጥ ታቁሮ የቀረ ወተት ካለ ነው።
ሌሎች ምክንያቶች ደግሞ የሚከተሉትን ያካትታሉ:-
❤️ የወተት መተላለፊያ ቱቦ መዘጋት፦ልጅ ጡት ሲጠባ / በሚመገቡበት ጊዜ ሙሉ በሙሉ ባዶ ካላደረገ የወተት ቱቦዎችዎ ሊደፈን ይችላል። መደፈኑ ወተት እንዲከማች ስለሚያደርግ ኢንፌክሽን እንዲፈጠር ያደርጋል።
❤️ ባክቴሪያ ወደ ጡትዎ መግባት፦ የቱት ጫፍ ላይ መሰንጠቅ ካለ ባክቴሪያ ከቆዳዎና ክልጁ አፍ ወደ ጡትዎ በወተት መተላለፊያ ቱቦ ቀዳዳ በኩል ይገባል። ይህ ሲጠባ ባዶ ያልሆነና ታቁሮ የቀረ ወተት ካለ ለባክቴሪያ መራባት እድል ይሰጣል።

አድራሻችን፦ ቦሌ ሩዋንዳ ከሩዋንዳ ኤምባሲ ጎን ሲሆን በተጨማሪም እኛን ለማግኘት ከፈለጉ የሚከተሉትን ይጠቀሙ
❤️https://t.me/sturaelclinic
❤️https://www.instagram.com/sturaelclinic
❤️https://www.sainturaelclinic.com
❤️9424
❤️+251-940464646 /0940565656 /0913349301 +251-116662556
/0116663741
❤️Rwanda St Just Beside Rwanda Embassy Addis Ababa Ethiopia.
❤️https://sturaelclinic@gmail.com

Telegram (https://t.me/sturaelclinic)
St. Urael Internal Medicine Clinic
ይህ የቅዱስ ኡራኤል የዉስጥ ደዌ ስፔሺያሊቲ ክሊኒክ ቻናል ነዉ።
አድራሻ፡- አዲስ አበባ፣ከ ቦሌ ወደ ቦሌ ሚካኤል በሚወስደዉ

Share with: