094 046 4646/0940 565656    
info@sainturaelclinic.com
Follow Us:

View Blog

አስም

ክፍል ሁለት

አስም በተደጋጋሚ ሲርሲር ማለት፣ትንፋሽ ማጠር ፣ የደረት ላይ ምቾት ያለመሰማት፣ ጠዋትና ማታ ሳል እንዲኖር የሚያደርግ ህመም ነዉ። አስም አስፈላጊዉን መድሃኒት በመዉሰድና አስምን ሊቀሰቅሱ የሚችሉ ነገሮችን በመለየትና በመከላከል ልንቆጣጠረዉ እንችላለን።

የህክምና ባለሙያ ማማከር የሚገባዎ መቼ ነዉ

ከፍተኛ የአስም ህመም ለህይወት አስጊ ሊሆን ይችላል። ስለሆነም የሚከተሉት ምልክቶች ካለዎ ድንገተኛ ህክምና የሚያስፈልግበት ጊዜ ነዉ። እነርሱም

·         የትንፋሽ ማጠር በድንገት እየተባባስ ከመጣ ወይም ሲተነፍሱ ሲር ሲር ማለት

·         ለድንገተኛ ማፈን የሚዉሰደውን የአስም መድሃኒት ወስደሁ ለዉጥ ከሌለዉ

·         መጠነኛ እንቅስቃሴ በሚያደርጉበት ወቅት የትንፋሽ ማጠር መታየት

አስምን መከላከል

ምንም እንኳ አስምን መከላከል የሚያስችል መንገድ ባይኖርም አስም ያለባችዉ ሰዎች ድንገተኛ የአስም ምልክቶች በመከታተል አስም አንዲቀሰቀስ የሚያደርጉትን ነገሮች መከላከል ያስፈልጋል። ይህም

·         የአስምዎን የድርጊት መርሃ ግብር ይከተሉ፦ አስም ቀጣይነት ባለዉ ሁኔታ የማይቋረጥ ክትትልና ህክምና የሚያስፈልገው ህመም ነው። የአስም ህክምናዎን መቆጣጠር ህይወትዎን ያለህመም እንዲመሩ ያደርግዎታል። ስልሆነም ሀኪምዎ በሚያዝልዎት መሰረት መድሃኒትዎን ይከታተል።

·         የአስም ቀስቃሾችን ለይቶ ማወቅ እና ማስወገድ፦ ከአበባ ብናኝ እና ሻጋታ እስከ ቀዝቃዛ አየር እና የአየር ብክለት ድረስ በርከት ያሉ ከቤትውጭ ያሉ የሚቆጠቁጡና  አለርጂን የሚቀሰቅሱ ነገሮች( አለርጂኖች)አሉ። አስምዎን የሚያመጡብዎ ወይም የሚያባብሱብዎ ነገሮች ምን እንደሆኑ ይወቁ ፣ ከዚያም እነዚያን ቀስቃሾች ለማስወገድ እርምጃዎችን ይውሰዱ።

·         የአተነፋፈስ ሁኔታዎን ይከታተሉ፦ አስምዎ ሊቀሰቀስብዎ መሆኑን ቅድመ- ማስጠንቀቂያ የሆኑ ምልክቶች እንደ ሲር ሲር ማለትና ትንፋሽ ማጠር  ያሉ ካሉ ማወቅና መከታተል።

·         የአስም መቀስቀስ ምልክቶችን ቀድመው መለየትና ማከም፦ በቶሎ እርምጃ ከወሰዱ ከባድ የአስም መቀስቀስ ወይም ድንገተኛ ጥቃት የመድረስ ዕድሉ አነስተኛ ነው። አስሙን ለመቆጣጠርም ብዙ መድሃኒቶች ላያስፈልግዎ ይችላል።

·         መድሃኒትዎን በታዘዘልዎ መሰረት ይዉሰዱ፦ የአስም ህመምዎ እየተሻሎት ቢሆንም የህክምና ባልሙያዎን ሳያማክሩ መድሃኒትዎ ላይ ለውጥ አያድርጉ። ሀኪምዎ ጋ ሲቀርቡ እየወሰዱያሉትን መድሃኒቶች ይዘዉ ይሂዱ። ሐኪምዎ መድሃኒቶችዎን በትክክል እየተጠቀሙና ትክክለኛውን መጠን መውሰድዎን ለማረጋገጥ ይችላል።


Share with: