094 046 4646/0940 565656    
info@sainturaelclinic.com
Follow Us:

View Blog

የታይፎይድ ህመም

የታይፎይድ በሽታ ሳልሞኔላ ታይፊ በተባለው ባክቴሪያ ምክንያት የሚመጣነ ብዙዉን ጊዜ በተበከለ ዉሃና ምግብ  የሚተላለፍ ለሕይወት አስጊ የሆነ ኢንፌክሽን ነው።  እንደ የአለም ጤና ድርጅት መረጃ ከሆነ በየዓመቱ ከ 11 እስከ 20 ሚሊዮን የሚገመቱ ሰዎች በታይፎይድ በሽታ የሚታመሙ ሲሆን ከ 128 ሺህ እስከ 161 ሺህ የሚገመቱ ሰዎች  ደግሞ በየዓመቱ በታይፎይድ ምክንያት ይሞታሉ።

የመተላለፊያ መንገዶች

ሳልሞኔላ ታይፊ ባክቴሪያ መኖር የሚችላዉ በሰዎች ውስጥ ብቻ ነው። የታይፎይድ ህመም ያለባቸው ሰዎች ተህዋሲያኑን (ባክቴሪያዉን) በደማቸውና በአንጀታቸው ውስጥ ይይዛሉ። ታይፎይድ ብዙውን ጊዜ በተበከለ ምግብ ወይም ውሃ እንዲሁም በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር የጠበቀ ግንኙነት መኖር ህመሙ ከአንዱ ወደሌላዉ ይተላለፋል። አንዴ በሳልሞኔላ ታይፊ ተህዋሲያን የተበከለ ዉሃ ከጠጡ ወይም ምግብ ከተመገቡ በኋላ ተዋሲያኑ እራሱን በሰዉነታችን ዉስጥ አባዝቶ በደም ዉስጥ ይሰራጫል።

የህመም ምልክቶች

·         ከፍተኛ ትኩሳት

·         ድካም

·         የራስምታት

·         ማቅለሽለሽ

·         የሕዕድ ሕመም(ቁርጠት)

·         የሆድ ድርቀት ወይም ተቅማጥ

·         የስዉነት ላይ ሽፍታ

·         የጡንቻ ህመም

·         ማላብ

·         ደረቅ ሳል

·         የምግብ ፍላጎት መቀነስና ክብዳት መቀነስ

ህመም እየቆየ ከመጣና ህክምና ካላገኙ የሚከተሉት ሊታዩ ይችላሉ

·         መቃዠት

·         ከመጠን ያለፈ መደካክምና እራስን መሳት፤ ይህ በህክምናዉ ታይፎይድ ስቴት ይባላል።



Share with: