ክፍል 2
ለታይፎይድ ህመም ተጋላጭ እነማናቸዉ
• ምንም እንኳን በአጠቃላይ ከአዋቂዎች ጋር ሲነፃፀሩ ቀለል ያሉ የህመም ምልክቶች ቢኖራቸውም በዓለም ዙሪያ ሕፃናት በበሽታው የመያዝ ዕድላቸው ከፍተኛ ነው
• በበሽታው ከተያዘ ወይም በቅርቡ በታይፎይድ በሽታ ከተያዘ ሰው ጋር የቅርብ ግንኙነት ያለዉ ሰዉ
• በፍሳሽ የተበከለ ውሃ የሚጠጡ ሰዎች
የታይፎይድ በሽታ የሚያመጣቸዉ የጎንዮሽ ጉዳቶች
1. የአንጀት መድማት
የአንጀት መድማትና የአንጀት ላይ ቃዳዳዎች መፈጠር ታይፎይድ ከሚያመጣቸዉ ከባዱ የጎንዮሽ ጉዳቶች ዉስጥ ዋነኛዉ ነዉ። ይህ አንድ ሰዉ በታይፎይድ በተያዘ በሶስተኛዉ ሳምንት የሚከሰት ነዉ። ይህ በትንሹ ወይም ትልቁ አንጀት ላይ የሚከሰት ነዉ። ህመሙም ከባድ የሆድ ህመም ፣ ማቅለሽለሽ ፣ ማስታወክና የደም ዝውውር ኢንፌክሽን (ሴፕሲስ) ሊያስከትል ይችላል። ይህ ለሕይወት አስጊ የሆነ ውስብስብ ሕክምና ችግር ስለሆን ወዲያውኑ ሕክምና ማግኘት ይስፈልጋል።
2. ሌሎች ሊከሰቱ የሚችሉ የጎንዮሽ ጉዳቶች
· የልብ ጡንቻዎች መቆጣት( ማዮካርዳይቲስ)
· የልብ የዉስጥ ግድግዳዎችና ቫልቮች ሽፋን መቆጣት ( ኢንዶካርዳይቲስ)
· የሳንባ ምች
· የቆሽት መቆጣት
· የኩላሊት ወይም ፊኛ እንፌክሽን
· የአንጎል እና የህብለሰረሰር በዙሪያዉ ያለው ሽፋንና ፈሳሽ ኢንፌክሽን እና እብጠት ( ሜኒንጃይትስ)
· የስነልቦና ችግሮች ናቸዉ
የታይፎይድ ህክምና
ለታይፎይድ ህመም ብቸኛው ውጤታማ ሕክምና ፀረ- ባክቴሪያ መድሃኒት (አንቲባዮቲክ) መዉሰድ ነዉ። በብዛት ከሚታዘዙት መድሃኒቶች ዉስጥ ዋነኛዉ ሲፕሮፍሎክሳሲልን የተባለዉ ፀረ- ባክቴሪያ መድሃኒት ሲሆን መድሃኒቱን ከመግዛትዎ በፊት ምርምራ ማድረግና የህክምና ባለሙያዎ ሊያዝልዎ ይገባል። ከመሃኒቱ በተጨማሪ በቂ ፈሳሽ መጠጣት የሚያስፈልግ ሲሆን ይህም በትኩሳትና በተቅማጥ ምክንያት ሊመጣ የሚችለዉን የሰዉነት ፈሳሽ ምጣኔ መዛባትን ለመከላከል ይረዳል።