ክፍል 3
የንጽህና ጉድለትና የንፁህ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት እጥረት ባለባቸው ቦታዎች ታይፎይድ ህመም የተለመደ ነው። የንፁህ ውሃ አቅርቦትና በቂ የአካባቢና የግል ንፅህና ፤ የምግብ አዘጋጆችና አስተናጋጆ ንፅህናና የታይፎይድ ክትባት የታይፎይድ ህመምን በመከላከል ረገድ ውጤታማ ናቸው። ስለሆነም ንፁህ የመጠጥ ውሃ ፣ የተሻሻለ ንፅህናና ለታይፎይድ ህሙማን በቂ የህክምና እንክብካቤ ማድረግ የታይፎይድ ህመምን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ይረዳሉ።
• የእጅዎን ንፅህና መጠበቅ፦ የታይፎይድ ህምመ የሚያመጡ ተዋህሲያንን ለመከላከልና ለቆጣጠር የሚረዳዉ በጣም ጥሩዉ መንገድ እጅን በዉሃና በሳሙና በተደጋጋሚ መታጠብ ነዉ።
• ንፅህናዉ ያልጠበቀ ዉሃ ከመጠጣት መቆጠብ፦ የታይፎይድ ህመም ሥር በሰደደባቸው አካባቢዎች የተበከለ የመጠጥ ውሃ ዋነኛዉ ችግር ነው። ስለሆነም የመጠጥ ውሃዉ ንፅህናና ደህንነት አጠያያቂ ከሆነብዎ ዉሃዉን አፍልተውና አቀዝቅዘዉ ይጠጡ አሊያም ፀር-ተዋሲያን የዉሃ ማከሚያ ኬሚካሎችን ይጠቀሙ።
• ጥሬ አትክልትና ፍራፍሬ አይመገቡ፦ አትክልትና ፍራፍሪዎች ንፁህ ባልሆነና በተበከል ዉሃ የታጥቡ ሊሆኑ ይችላሉ ። አንደሰላጣ ያሉ በጥሬ የሚበሉና ሊላጡ የማይችሉ ፍራፍሪዎችን በትክክልና በንፅህና የታጠቡ መሆናቸዉን ከማረጋገጥዎ በፊት አለመመገብ
ሌሎችን ከኢንፌክሽኑ ለመከላከል
እርስዎ በታይፎይድ ህመም ተይዘዉ ከሆነ ሌሎችን ከኢንፌክሽኑ ለመከላከል የሚከተሉትን እርምጃዎች ይዉሰዱ
• መድሃኒትዎን በአግባቡ መዉሰድ ፦ የታዘዘልዎን መድሃኒቶች በአግባቡ ወስደሁ መጨረስዎን ያረጋግጡ
• የእጅ ንፅህናዎን በአግባቡ መጠበቅ፦ ኢንፌክሽኑን ወደ ሌሎች እንዳያስተላልፉ ማድረግ የሚችሉት ብቸኛውና በጣም አስፈላጊው ነገር ይህ ነው። ( በተለየይ ከመዳጃ ቤት መልስና ከመመገብዎ በፊት)
• ምግብ ከማዘጋጀት መቆጠብ፦ የህክምና ባለሙያዎ ከአሁን በኋላ ለሌሎች በሽታዉን አስተላላፊ አይደሉም እስከሚልዎ ድረስ ለሌሎች ምግብ ከማዘጋጀት ይቆጠቡ ። በምግብ አገልግሎት ኢንዱስትሪ ውስጥ ወይም በጤና አጠባበቅ ተቋም ውስጥ የሚሰሩ ከሆነ ምርመራዎች ከእንግዲህ የታይፎይድ ባክቴሪያዎችን እንደማያስተላልፉ እስኪያዩ ድረስ ወደ ሥራ እንዲመለሱ አይመከሩም፣።