094 046 4646/0940 565656    
info@sainturaelclinic.com
Follow Us:

View Blog

የአጥንት መሳሳት (ኦስቲዮፖሮሲስ)

ክፍል አንድ

የአጥንት መሳሳት አጥንት እንዲዳከምና እንዲሰበር ያደርጋል-- ይህም ማለት መዉዳቅ ወይም ሌላው ቀርቶ እንደ ማጎንበስ ወይም ማሳል ያሉ መለስተኛ ወይም ቀላል እንቅስቃሴዎች  ስብራት ሊያስከትሉ ይችላሉ። ከአጥንት መሳሳት ጋር የተዛመዱ የአጥንት ስብራት ብዙውን ጊዜ በጭን ፣ በእጅ አንጓ ወይም በአከርካሪ አጥንቶች ላይ ይከሰታሉ። አጥንት ያለማቋረጥ እየተነሳ ወይም ያረጀዉ በአዲስ እራሱን እየተካ የሚሄድ ህያው ህዋስ ነው። የአጥንት መሳሳት የሚከሰተው የአዲሱ አጥንት መዘጋጀት/መፈጠር ከአሮጌ አጥንት መወገድ ጋር እኩል የማይሄድና የማይጣጣም ከሆነ ነዉ። የአጥንት መሳሳት በሁሉም የሰዉ ዘር በወንዶችና ሴቶች ላይ ተጽዕኖ ያሳድራል።

የህመም ምልክቶች

በመጀመሪያ የአጥንት መሳሳት ጊዜያት ወይም የህመም  ደረጃዎች ውስጥ ምንም የህመም ምልክቶች ላይታዩ ይችላሉ። ነገር ግን አጥንቶችዎ በአጥንት መሳሳት ምክንያት ከተዳከሙ በኋላ የሚከተሉትን ምልክቶች ሊያዩዎት ይችላሉ-

የህመም ምልክቶች

·         የቁመት ማጠር ወይም መቀነስ፦ በተወሰኑ ሴንቲሜትሮች የቁመት መጠን መቀነስ

·         የሰዉነት አቋም  ወይም ፖስቸር መለወጥ ፦ ማጎንበስ ወይም ወደ ፊት መታጠፍ

·         የትንፋሸ መጠር፦ የአከርካሪ አጥንት ዲስኮች መጨመቅ ወይም መጠን መቀነስ ምክንያት አነስተኛ የሳንባ የመያዝ አቅም መቀነስ

·         የአጥንት ስብራቶች መከሰት

·         በታችኛዉ የጀርባ አጥንት ላይ ህመም መኖር ናቸዉ



Share with: