094 046 4646/0940 565656    
info@sainturaelclinic.com
Follow Us:

View Blog

ለአጥንት መሳሳት አጋላጭ ነገሮች

ክፍል ሁለት

ለአጥንት መሳሳት አጋላጭ ነገሮች    

1.         የማይለዋወጡ አጋላጭ ነገሮች

•           ፆታ፥- ከወንዶች ይልቅ ሴቶች ለችግሩ ተጋላጭ ናቸዉ

•           ዕድሜ፦ ዕድሜዎ በጨመረ ቁጥር በአጥንት መሳሳት ችግር የመጠቃት እድልዎ እየጨመረ ይሄዳል

•           በቤተሰብ መሰል ችግር መኖር፦ የአጥንት መሳሳት ችግር ያለበት ወላጅ ወይም ወንድም ወይም እህት መኖር በተለይ እናት ወይም አባት

•           የሰዉነት መጠን፦ የሰዉነት መጠናቸው ትንሽ ወይም አነስተኛ የሆኑ ሰዎች ለአጥንት መሳሳት ችግር የመጋለጣቸዉ ሁኔታ ከፍተኛ ነዉ።

2.         የሆርሞን መጠን፦

የአጥንት መሳሳት ችግር በጣም የበዛ ወይም በጣም ያነሰ የሆርሞን መጠን ሲኖር ሊከሰት ይችላል። ከነዚህም ዉስጥ

•           ከፆታ ጋር የተገናኙ ሆርሞኖች፦ ከፆታ ጋር የተገኛቹ ሆርሞኖች መጠን አነስተኛ ከሆኑ ለአጥንት መሳሳት ችግር ይዳርጋሉ። ሴቶች ላይ ከወር አበባ ዑደት መቋረጥ ጋር ተያይዞ የሚከሰተዉ የኢስትሮጂን ሆርሞን መቀነስ በሴቶች ላይ ለአጥንት መሳሳት ችግር መከሰት ዋነኛ መንስዔ ነዉ። በወንዶች ላይ የፕሮስቴት ሆርሞን መቀነስ ዋነኛ መንስዔ  ነዉ።

•           የታይሮይድ ችግሮች፦ የታይሮይድ ሆርሞን መጠን ከፍተኛ መሆን ለአጥንት መሳሳት ችግር ይዳርጋል

•           ሌሎች ዕጢዎች፦ የፓራታይሮይድና አድሬናል ዕጢዎች ከመጠን በላይ ሆርሞን ማመንጨት

3.         ከአመጋገብ ጋር የተያያዙ ችግሮች

አነስተኛ የካልሲየም መጠን፦ ለረጅም ጊዜ አነስተኛ የሰዉነት የካልሲየም መጠን  መኖር ለአጥንት መሳሳት ችግር ይዳርጋል። ዝቅተኛ የካልሲየም መጠን ለአጥንት ጥግግት ( ዴንሲቲ) መቀነስ ፣ ለአጥንት ያለወቅቱ/ጊዜዉ መሳሳትና  ለአጥንት ስብራት መጨመር አስተዋፅኦ ያደርጋል።

የምግብ አመጋገብ ችግር፦ የምግብ አመጋገብ በከፍተኛ ሁኔታ መገደብ ወይም ከመጠን ያለፈ መቀነስ እና በወንዶችም ሆነ በሴቶች ከመጠን በላይ ክብደት መቀነስ ወይም የሰዉነት ክብደት ከልክ በታች መሆን  አጥንትን ያዳክማል

4.         መድሃኒቶች

እንደ ፕሪደንሴሎንና ኮርቲሶን ያሉ መድሃንቶችን ለረጅም ጊዜ መዉሰድ ለአጥንት መሳሳት ችግር ይዳርጋል። በተጨማሪም ለሚጥል በሽታ፣ ለአሲድ ሪፍሌክስ ፣ ለካንሰርና በአካል ንቅለተከላ ወቅት የሚሰጡ መድሃኒቶች ለአጥንት መሳሳት ችግር ይዳርጋል።

5.         የዉስጥ ደዌ ችግሮች

•           የኩላሊት ውይም ጉበት ችግር

•           ካንሰር

•           ሪሄማቶይድ አርትራይትስ

•           ኢንፈላማቶሪ ባወል ዲዚዝ ( የአንጀት ችግር)

6.         የአኗኗር ዘይቤ ምርጫዎች

•           እንቅስቃሴ አልባ አኗኗር፦ ብዙ ጊዜ ተቀምጠው የሚያሳልፉ ሰዎች የበለጠ ንቁ ከሆኑት ይልቅ ለአጥንት መሳሳት ችግር የመያዝ ዕድላቸው ከፍተኛ ነው

•           ከመጠን ያለፈ አልኮል መጠጣት፦ በቀን ከሁለት በላይ የአልኮል መጠጦችን አዘውትሮ መጠቀም ለአጥንት መሳሳት የመጋለጥ እድልን ይጨምራል

•           ሲጋራ ማጨስ፦ ትንባሆ መጠቀም ለደካማ አጥንቶች አስተዋጽኦ ያደርጋል።


Share with: