ክፍል አንድ
በእግርዎ፣ እጅዎና ሌሎች የሰዉነት ክፍልዎ ላይ የመደንዘዝ ስሜት አልዎ? ይህ ስሜት ካለዎ የዉስጥ ደዌ ችግር ምልክት ሊሆን ስለሚችል የህክምና በለሙያዎን ያማክሩ።
የመደንዘዝ ስሜት በሰዉነታችን አካል ላይ በተወሰነ አካባቢ የስሜት ማጣት በሚከሰትበት ወቅት የሚታይ ነዉ። ይህ አንዳንድ ጊዜ በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ ስሜቱ መጥፋት ሊታይ ይችላል። ይህ ችግር ብዙውን ጊዜ እንደ ማቃጠል ወይም እንደ መርፌ መዉጋት ስሜት ያሉ ሌሎች የስሜት ለውጦችን ለመግለጽም ያገለግላል። የመደንዘዝ ስሜት በአንደኛው የሰውነት ክፍል በአንድ በኩል በአንድ ነርቭ ላይ ሊከሰት ይችላል ፣ ወይም በሁለቱም የሰዉነታችን ክፍሎች ላይ በተመጣጠነ ሁኔታ ሊከሰት ይችላል። ምንም እንኳን የብዙ የተለያዩ የሕክምና ችግሮች የተለመዱ ምልክቶች ቢሆኑም በአብዛኛዉን ጊዜ የሚታየዉ በሰውነት ውስጥ በነርቮች ላይ ችግር መኖር ምልክት ነው።አብዛኛዎቹ የመደንዘዝ ስሜት የሚያመጡ ነገሮች ከባድ አይደሉም። በጣም ከባድ በሆኑ ሁኔታዎች ወቅት የመደንዘዝ ስሜት የጎንዮሽ ጉዳት ሊያስከትል ይችላል ለምሳሌ መደንዘዝ በሚከሰትበት ቦታ የሆነ ነገር ሲያቃጥለንም ይሁን ሲወጋን ምንም አለመሰማት ካለዉ (ለምሳሌ ከከፍተኛ ሙቀት ሕመሙ የማይሰማ ከሆነ ቃጠሎዎችን ያስከትላል) ወይም የአካል ክፍሎች ላይ ምን እየሆነ እንዳለ አለማወቅ (ለምሳሌ በሚወድቁበት ወቅት የእግሮችዎን አቀማመጥና አቅጣጫ ማወቅ የማይችሉ ከሆነ) ከፍትኛ ችግር ሊያመጣ ይችላል። እንዲሁም እንደ የስኳር በሽታና ሌሎች እንደ መልትፕል ስክለሮሲስ የመሳሰሉ ከባድ ሥር የሰደዱ በሽታ ምልክት ሊሆን ይችላል
የመደንዘዝ ስሜት እንዴት ሊከሰት ይችላል
የመደንዘዝ ስሜት እንዲከሰት የሚያደርጉ የሚችሉ ብዙ ምክንያቶች አሉት። በነርቭ ወይም በነርቮች ላይ የሚከሰት ችግር አብዛኛውን ጊዜ ምልክቱን ያስከትላል። አንድ ነርቭ ሲጎዳ ወይም የሆነ ነገር ሲጫነዉ ፣ የሰውነት መደበኛ ስሜቶችን የመሰማትን ችሎታ ያደናቅፋል
አንዳንድ የመደንዘዝ ስሜት ምክንያቶች በአከርካሪው ውስጥ እና በአከባቢው ነርቮች ላይ ያልተለመደ ጫና የሚያስከትል ነገር ሲከሰት የሚመጣ ነዉ። የመደንዘዝ ስሜት የሚመጣው በነርቮች መጎዳት ፣ መቆጣት ወይም የሆ ነገር ነርቩን ሲጫነዉ ነው። የመደንዘዝ ስሜት የሚከሰተዉ በአንድ ነጠላ የነርቭ ቅርንጫፍ ወይም በርካታ ነርቮች ሊጎዱ ይችላሉ።
ይህንን የመደንዘዝ ስሜት ሊያስከትሉ የሚችሉ ሁኔታዎች የሚከተሉትን ያካትታሉ:
· በአጥንት መሳሳት ምክንያት የጀርባ ወይም አከርካሪ አጥንት መሰበርና ነርቭን መጫን
· በህብለ-ሰረሰሩን የተጫነዉ ነገር መኖር
· የዲስክ መንሽራተት ሲኖር
· በአርትራይተስና በአጥንት ማደግ ምክንያት ነርቭን ቆንጥጦ መያዝ
በሌሎች የህክምና ችግሮች ወይም ህመሞች ምክንያት የሚከሰት
· የስኳር ህመም
· እንደ ኤች አይቪ ያሉ ኢንፌክሽኖች መኖር
· መድሃኒቶች
· የኩላሊት ህምመ
· መልትፕል ስክለሮሲስ
· ስትሮክ
· አርትራይትስ
· ዕጢ
· የካንሰር ወደ አከርካሪ አጥንት መዛመት
· ለመርዛማ ነገሮች መጋለጥ ናቸዉ።