ከመደንዘዝ ስሜቱ ጋር በእግርዎና መዳፉ ላይ አብሮ የመንዘርና የማሳከክ ስሜት ሊኖር ይችላል።
በእግራቸውና በአግር መዳፍ ውስጥ የመደንዘዝ ስሜት ያላቸው ብዙ ሰዎች አንድ አንድ ጊዜ ወይም አለፍ ገደም እያለ የሚታይ ተጨማሪ ምልክቶች ሊያጋጥማቸዉ ይችላል። ከነዚሂም ዉስጥ ፦
· የመንከስ ስሜት
· ማቃጠል
· የመንዘር
· የማሳከክ
· ቆዳዎ ስር የሚሄድ ነገር ያለ መምሳል ናቸዉ።
ህክምና
ለረጅም ጊዜ ለቆየ የመደንዘዝ ስሜት የሚደረግ ህክምና የሚከተሉትን ሊያጠቃልል ይችላል
· አንታይዲፕሬሳንት መድሃኒቶች፦
· ኮቲኮስቴሮይዶች
· ጋባ ፔንቲነና ፕሪጋባሊን የሚባሉ መድሃኒቶች
የቤት ዉስጥ ህክምናዎች
ምቾት የሚነሳን የመደንዘዝ ስሜትን ለማስታገስ የሚረዱ የቤት ውስጥ ህክምናዎች
· እረፍት፦ የእግር መደንዘዝን የሚያስከትሉ ብዙ ችግሮች እረፍት በማድረግ ህመሙ ይሻሻላል።
· በረዶ ቦታዉ ላይ መያዝ፦ በረዶ በነርቮች ላይ ጫና ሊፈጥር የሚችል እብጠትን ለመቀነስ ይረዳል
· ሙቀት፦ ሙቀት አንዳንድ ጊዜ ነርቮች ላይ ጫና ሊያሳድሩ እና የመደንዘዝ ስሜትን ሊያስከትሉ የሚችሉ ጠንካራ ፣ የታመሙ ወይም የተጨናነቁ ጡንቻዎችን ለማቅለል ይረዳል። ሆኖም ፣ ይህ እብጠትንና እግሮችን ከመጠን በላይ ከማሞቅ ይቆጠቡ ፣ ምክንያቱም ይህ እብጠትን ሊያባብሰውና ህመም እና መደንዘዝ ሊያስከትል ይችላል።
· ማሳጅ ማደረግ፦ የደነዘዘ እግሮችንና የእግሮ መዳፎችን ማሸት የደም ፍሰትን ለማሻሻል ይረዳል ፤ ይህም የህመም ምልክቶችን ሊቀንስ ይችላል።
· የአካል ብቃት እንቅስቃሴ፦ ተገቢዉን የአካል ብቃት እንቅስቃሴ አለማድረግ ልብንና የደም ሥሮ ደካማእንዲሆኑ ስለሚያደርግ፣ የደምን ወደ ታችኛው እግሮች የመርጨት አቅማቸውን ይቀንሳል። የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎች የደም ፍሰትን ሊጨምሩና ሥር የሰደደ እብጠት ወይም ህመምን ሊቀንሱ ይችላሉ።
· ድጋፍ ሰጪ መሣሪያዎች፡- ብሬስና በልዩ ሁኔታ የተነደፉ ውይም የተዘጋጁ ጫማዎች በጉዳት፣ ካርፓል ታናል ሲንድሮምና በጠፍጣፋ እግር ምክንያት የሚከሰተውን የነርቭ ላይ ጫናን ለመቀነስ ይረዳሉ።
· አልኮልን መቀነስ ወይም ከአልኮል መራቅ፦ አልኮሆል የነርቭ መጎዳት እና የመደንዘዝ ስሜትን ሊያስከትሉ የሚችሉ መርዛማ ንጥረ ነገሮችን ይዟል። እንዲሁ አልኮሆል ብዙውን ጊዜ ሥር የሰደደ ህመምንና የእብጠት ህመም ምልክቶች ያባብሳቸዋል፤ አልፎ ተርፎም የሕመም ምልክቶችን ያስከትላል።
· በተለምዶ የእንግሊዝ ጨዉ በሚባለዉ መታጥብ( Epsom salt baths)፦ የእንግሊዝ ጨዉ በዉስጡ ማግኒዝየም አለዉ። መግኒዝየም ደግሞ የደም ዝዉዉርን ለማሻሻል ይረዳል።
· ጭንቀትን ወይም ዉጥረትን መቀነስ፦ ውጥረት እንዲሁ የማዕከላዊው የነርቭ ሥርዓት በመዛባት የህመ ምልክቶቹ የከፋ እንዲሆኑ ያደርጋል። ስለሆነም ጭንቀትን መቀነስ
· ጤናማና የተመጣጠነ ምግብ መመገብ፦ የምግብ ዕጥረት በተለይ ቫይታሚን ቢ የምግብ እጥረት መኖር የነርቭ ላይ ጉዳት እንዲከሰት በማድረግ ለመደንዘዝ ስሜት መከሰት ምክንያት ይሆናል። ስለሆነም ቫይታሚኖችን ጨምሮ የተመጣጠኑ ምግቦችን መመገብ ለነርቭ ጤንነት መልካም ነዉ።
· እንቅልፍ፦ ከእግርና ከእግር መዳፍ መደንዘዝ ጋር የተዛመዱ ብዙ ሥር የሰደዱ ችግሮች በትክክለኛ እንቅልፍ እጦት ምክንያት እየተባባሱ ይሄዳሉ።