094 046 4646/0940 565656    
info@sainturaelclinic.com
Follow Us:

View Blog

የሳንባ የደም ቅዳ መዘጋት ( ፑልሞናሪ ኢምቦሊዝም- Pulmonary embolism)

ያልታወቀ ወይም በድንገት የተከሰተ የትንፋሽ እጥረት ፣ የደረት ላይ ህመም ወይም ደም የቀላቀል አክታ ያለዉ  ሳል ካጋጠመዎት  የሳንባ የደም ቅዳ መዘጋት ሊሆን ስለሚችል አስቸኳይ የህክምና እርዳታ ያግኙ።

የሳንባ የደም ቅዳ መዘጋት በሳንባ ዉስጥ ባሉ በአንደኛዉ የደም ቅዳ ላይ የደም ዝዉዉር መዘጋት በሚፈጠርበት ወቅት የሚከሰት ነዉ። ይህ በብዛት የሚከሰተው በእግሮች ውስጥ ካሉ ትላልቅ የደም መልሶች ወይም አልፎ አልፎ ፣ በሌሎች የሰውነት ክፍሎች ውስጥ ካሉ ደም መላሽ ቧንቧዎች የረጋ ደም ከረጋበት ተነስቶ ወይም ተገንጥሎ ወደ ሳንባዎች በመጓዝ የሳንባ  የደም ቅዳዎችን በሚዘጋበት ወቅት ነዉ። የደም መርጋት ወደ ሳንባዎች የሚሄድን  የደም ፍሰት ስለሚዘጋ ፣ የሳንባ የደም ቅዳ መዘጋት  ለሕይወት አስጊ ሊሆን ይችላል። ይሁን እንጂ ችግሩ ሲከሰት ፈጣን ህክምና ማግኘት የሞት አደጋን በእጅጉ ይቀንሳል። በእግሮችዎ ውስጥ የደም መዘጋትን ለመከላከል እርምጃዎችን መውሰድ የሳንባ የደም ቅዳ መዘጋትን  ለመከላከል ይረዳዎታል።

የህመም ምልክቶች

በሳንባዎ ውስጥ ምን ያህል የሳንባ ክፍል እንደተጠቃ፣ የረጋዉ ደም መጠንና ሥር የሰደደ የሳንባ ወይም የልብ በሽታ እንዳለብዎት ሁኔታ የሳንባ የደም ቅዳ መዘጋት የህመም ምልክቶች  በከፍተኛ ሁኔታ ሊለያዩ ይችላሉ።

በብዛት የሚታዩ የህመም ምልክቶች፦

·         የትንፋሽ ማጠር፦ ይህ ምልክት በዋነኛነት በድንገት የሚከሰት ሲሆን ህመምተኛዉ እንቅስቃሴ ሲያደርግ እየባሰ ይሄዳል።

·         የደለት ህመም፦ ድንገተኛ የልብ ህመም ችግር እንደተከሰትብዎ አይነት ስሜት ሊሰማዎ ይችላል። ህመሙ ጠንካራ የዉጋት ስሜት ያልዉ ሲሆን ወደዉስጥ ሲተነፍሱ ይስማዎታል፣ ወደዉስጥ አየር በደንብ ስቦ ለማስገባት ያስቸግርዎታል። በተጨማሪም ህመሙ ሲያስሉ፣ሲታጠፉና ሲንበረከኩ ሊሰማዎ ይችላል።

·         ሳል፦ ሳሉ ደም የሆነ አሊያም ደም የተቀላቀለበት አክታ ሊኖርዎ ይችላል።

·         የራስምታት ወይም ማዞር

·         በከፍተኛ ሁኔታ ማላብ

·         ትኩሳት

·         ፋጣን ወይም  የተዛባ የልብ ምት

·         የእግር ላይ ህመም ወይም ማበጥ ወይም ሁለቱም በተለይ የእግርባት ላይ

·         የቆዳ ቀለም መቀየር ( ሲያኖሲስ) ናቸዉ


Share with: