094 046 4646/0940 565656    
info@sainturaelclinic.com
Follow Us:

View Blog

ለሳንባ የደም ቅዳ መዘጋት አጋላጭ ነግሮች

ምንም እንኳን ማንኛውም ሰው የደም መርጋት እና ቀጣይ ወደ የሳንባ ደም ቅዳ መዘጋት ችግር ሊያድግ ቢችልም የተወሰኑ ምክንያቶች አደጋዎን ሊጨምሩ ይችላሉ። እነሱም

1.      የህክምና ችግሮችና ህክምናዎቹ

እርስዎ ወይም ማንኛውም የቤተሰብዎ አባላት ቀደም ሲል የደም መልስ የደም መርጋት ወይም ይሳንባ ደም ቅዳ መዘጋት ችግር ከነበረ ለሳንባ ደም ቅዳ መዘጋት ችግር ከፍተኛ ነዉ። በተጨማሪም የተወሰኑ የህክምና ችግሮችና ህክምናዎቻቸዉ ችግሩን ሊያባብሱ ይችላሉ። ከነዚህም ዉስጥ

·         የልብ ህመም፦ የልብ ችግር በተለይ የልብ ድካም መኖር የደም መርጋት የመፈጠርን ያባብሳሉ

·         ካንሰር፦ የተወሰኑ ካንሰሮች በተለይ የአንጎል፣የቆሽት፣ የትልቁ አንጀት፣ የጨጓራ፣ የሳንባ የኩላሊትና የኦቫሪ መኖር የደም መርጋት ችግርን ይጨምራሉ

·         ቀዶ ጥገና፦ ለደም መርጋት ችግር መንስኤ ከሆኑት አንዱ ቀዶ ጥገና ነው። በዚህ ምክንያት ከከባድ ቀዶ ጥገና በፊትና በኋላ የደም መርጋትን ለመከላከል መድሃኒት ሊሰጥ ይችላል።

·         የደም መርጋት ላይ ተጽዕኖ የሚያሳድሩ ችግሮች፦ አንዳንድ በዘር የሚተላለፉ በሽታዎች በደም ላይ ተጽዕኖ ያሳድራሉ፤ ይህም ለደም መረጋት የበለጠ ተጋላጭ ያደርጋሉ።

·         የኮሮናቫይረስ በሽታ -ኮቪድ 19 (COVID-19)፦ የኮቪድ 19(COVID-19) ከባድ የህመም ምልክቶች ያላቸዉ ወይም ያጋጠማቸው ሰዎች ለሳንባ ደም ቅዳ መዘጋት ችግር የመጋለጥ እድላቸው ከፍ ያለ ነው።

2.     ለረጅም ጊዜ ያለመንቀሳቀስ

በእንቅስቃሴ -አልባነት ጊዜያት የደም መርጋት የመፍጠር ዕድሉ ከፍተኛ ነው ፣ ለምሳሌ ፦

·         ለረጅም ጊዜ በአልጋ ላይ መቆየት፦ ከቀዶ ጥገና በኋላ ፣ የልብ ድካም ፣ የእግር መሰበር ፣ ከአደጋ በኃላ ወይም በማንኛውም ከባድ በሽታ ተይዘዉ ረዘም ላለ ጊዜ በአልጋ ላይ ከቆዩ ለደም መርጋት የበለጠ ተጋላጭ ያደርግዎታል። እግሮችዎ ለረጅም ጊዜ ተዘርግተዉ ሲቆዩ ፣ የእግሮችዎ የደም መልስ የደም ዝዉዉር ወይም የደም ፍሰት ስለሚቀንስ ደም በእግሮችዎ ውስጥ ሊከማች ይችላል ፣ይህም የደም መርጋት ሊያስከትል ይችላል።

·         ረጅም ጉዞ፦ ለረጅም ሰዓታት በአውሮፕላን ወይም በመኪና ጉዞዎች  ጠባብ በሆነ ቦታ ላይ ተኮማትሮ መቀመጥ የእግሮችዎን የደም ፍሰትን ይቀንሳል ፣ ይህም ደም መርጋት መከሰት አስተዋጽኦ ያደርጋል።

3.     ሌሎች አጋላጭ ነገሮች መኖር

·         ሲጋራ ማጨስ፦ ምክንያቱ ብዙም ባይታወቅም ሲጋራ የሚያጨሱ ሰዎች በአንዳንድ ሰዎች ላይ የደም መርጋት ችግር አንዲከሰት ያደርጋል።

·         ከመጠን በላይ የሆነ የሰዉነት ክብደት፦ ከመጠን በላይ የሆነ የሰዉነት ክብደት መኖር የደም መርጋት አደጋን ይጨምራል - በተለይም ሌሎች አጋላጭ  ምክንያቶች ባሏቸው ሰዎች ላይ።

·         ኢስትሮጂን ሆርሞንን በተጨማሪነት የሚወስዱ፦ በተለይ ሲጋራ የሚያጨሱና ክብደትዎ ከመጠን በላይ ከሆነ በወሊድ መከላከያ ዉስጥ ያለዉ ኢስትሮጂን ወይም በሰዉነትዎ ዉስጥ የጎደለዉን የኢስትሮጂን ሆርሞንን ለመተካት በህክምና በለሙያዎች የሚሰጡ የኢስትሮጂን ሆርሞን ህክምናዎች ደም እንዲረጋ የሚያደርጉ ንጥረነግሮችን ይጨምራሉ

·         እርግዝና፦ በእርግዝና ወቅት የፅንሱ ክብደት በዳሌዎ ዉስጥ የሚያልፉ የደም መልሶች ላይ ጫና ስለሚፈጥር በእግሮችዎ ላይየደም ዘዝዉዉር እንዲቀንስ/እንዲዘገይ ያደርጋል። የደም ዝዉዉሩ ዘገምተኛ መሆን የደም መረጋት እንዲፈጠር ያደርጋል።

የሳንባ የደም ቅዳ መዘጋት ሊያስከትለዉ የሚችለዉ የጎንዮሽ ጉዳት

·         የሳንባ ደም ቅዳ መዘጋት ችግር  ለሕይወት አስጊ ሊሆን ይችላል።  ያልተመረመሩና ያልታከሙ የሳንባ የደም ቅዳ መዘጋት ምልክቶች ካላቸው ሰዎች መካከል አንድ ሦስተኛ የሚሆኑት በሳንባ የደም ቅዳ መዘጋት ምክንያት ሕይወታቸዉ ያልፋል። በጊዜ ምርመራ ተደርጎ ህክምና በአፋጣኝ ከተደረግ ግን የሞት መጠኑን መቀነስ ይቻላል።

·         የሳንባ ደም ቅዳ መዘጋት ችግር በሳንባ ዉስጥ ያሉ የደም ቅዳ ግፊት መጠን (የደም ግፊት) ሊጨምር ይችላል ፣ ይህ ሁኔታ በሳንባዎችዎ ውስጥና በቀኝ የልብ ክፍል ውስጥ ያለው የደም ግፊት በጣም ከፍ እንዲል ያደርጋል። ይህ  በልብዎ ላይ ጫና ስለሚፈጥር ልብን  ያዳክማል።



Share with: