ክፍል አንድ
የማጅራት ገትር በሽታ የአንጎልና ህብለ-ሰረሰርን የሚሸፍኑ የመከላከያ ሽፋኖች መቆጣት ወይም እብጠት ነው። አብዛኛውን ጊዜ እብጠቱ እንዲከሰት የሚያደርገዉ በአንጎልና በህብለ-ሰረሰር ዙሪያ ያለው ፈሳሽ በባክቴሪያ ወይም በቫይረስ ምክንያት ኢንፌክሽን በሚፈጠርበት ወቅት ነዉ። የማጅራት ገትር በሽታ በብዛት እንዲከሰት የሚያደርጉት ባክቴሪያና ቫይረሶች ናቸዉ። ብዙ አይነት ባክቴሪያዎች የማጅራት ገትር በሽታ የሚያመጡ ሲሆን ከነዚህም ዉስጥ ስትሬፕቶኮካል ኒሞኒየ፣ ሄሞፊለስ ኢንፉሌንዜና ንሴሪያ ሜኔንጅትድስ በብዛት ይጠቀሳሉ። ንሴሪያ ሜኔንጅትድስ ሜኔንጆኮካል ሜንንጃይትስን የሚያመጣዉ ባክቴሪያ ሲሆን በባክቴሪያ ምክንያት ለሚከሰተዉ ከፍተኛ ወረርሽን ምክንያት ነዉ።
የማጅራት ገትር በሽታ በምን ምክንያት ማወቅ አስፈላጊ ነው ምክንያቱም ህክምናው እንደ ምክንያት ይወሰናል።ሌሎች ምክንያቶችም ያሉ ሲሆን የሚከተሉትን ሊያካትቱ ይችላሉ፡-
· ፈንገስ
· ኬሚካል
· ካንሰር
· በአደጋ ምክንያትና
· በመድሃኒቶች የሚመጣ አለርጂ ናቸዉ።
አንዳንድ በቫይረስና በባክቴሪያ ምክንያት የሚከሰቱ የማጅራት ገትር በሽታዎች ተላላፊ ናቸው። ይህም ታማሚዉ በሚያስልበት፣ በሚያስነጥስበትና በንክክኪ አማካኝነት ሊተላለፉ ይችላሉ።
የህመም ምልክቶች
በቫይረስና በባክቴሪያ ምክንያት የሚከሰት የማጅራት ገትር በሽታ ምልክቶች መጀመሪያ ላይ ተመሳሳይ ሊሆኑ ይችላሉ። ይሁን እንጂ በባክቴሪያ ምክንያት የሚከሰት የማጅራት ገትር ምልክቶች አብዛኛውን ጊዜ በጣም የከፋ ናቸው። የህመም ምልክቶቹ
· የራስ ምታት
· ትኩሳት
· የማጅራት መገተር
· ማንቀጥቀጥ
· ለደማቅ ብርሃን ሲጋልጡ ማየት መቸገር
· ማቅለሽለሽና ማስታወክ
· የአዕምሮ ሁኔታ መቀያየር
· ብርድ ብርድ ማለት
· እንቅልፍ እንቅልፍ ማለት
· የቆዳ ላይ ሽፍታ
· የምግብ ፍላጎት መቀነስና የመሳሰሉት ናቸዉ።