094 046 4646/0940 565656    
info@sainturaelclinic.com
Follow Us:

View Blog

የአፍ ጤንነትን ለመጠበቅ የሚሞከሩ 9 ነገሮች

ጠንካራ ጥርሶችን ለመጠበቅ ማድረግ የሚችሏቸው አንዳንድ ነገሮች የሚከተሉት ናቸዉ።

·         የአፍ ንፅህናን በጥሩ ሁኔታ መጠበቅን ይለማመዱ ፦  ጥርስዎ ላይ የሚለጠፉ በገሮችን  ለማስወገድ በቀን ሁለት ጊዜ ጥርሶችን በደንብ ይቦርሹ እንዲሁም በየቀኑ በጥርሶች መካከል የሚቀርን የምግብ ቅንጣቶች በማስወገጃ የፅዱ።

·        ሲጋራ ከማጨስ ይቆጠቡ። እያጨሱም ከሆን ለማቆም ይሞክሩ

·        የአልኮሆል መጠጥን ይገድቡ

·        የስኳር በሽታ ካለብዎ በሽታውን ወይም የስኳርዎን መጠን መቆጣጠር ያስፈልጋል። ይህን ማድራግ ሌሎች አንደ የድድ ህመሞች ያሉ የጎንዮሽ ጉዳቶችን ለመቀነስ ይረዳል። የድድ በሽታን ማከም የደም ስኳር መጠንዎን ለመቀነስ ይረዳል

·        መድሃኒት እየወሰዱ ከሆነና መድሃኒትዎ የአፍ ድርቀት  የሚያስከትል ከሆነ ፣ ሀኪምዎን በማማከር መድሃኒትዎ እንዲለወጥልዎ ማድረግ። የአፍ ድርቀቱን ማስቀረት የማይችሉ ከሆነ  ብዙ ውሃ ይጠጡ ፣ ስኳር የሌለውን ማስቲካ  ያኝኩ ፣ የትንባሆ ምርቶችንና አልኮልን ያስወግዱ።

·        ፍሎራይድ ያለበት ውሃ ይጠጡ እንዲሁም ፍሎራይድ ባለዉ የጥርስ ሳሙና አፍና ጥርስዎን ያፅዱ።

·        ቢያንስ በዓመት አንድ ጊዜ የጥርስ ሀኪምዎን ይጎብኙ:- የተፈጥሮ ጥርስ ባይኖርዎትም ወይም ያሎት አርቴፊሻል ጥርስ ቢሆንም እንኳ ይህን ከማድረግ አይቆጠቡ

·        በድንገት የመቅመስና የማሽተት ለውጦች ከታዩብዎ ሐኪምዎን ያማክሩ።

·        በእድሜ የገፉ አረጋዉያንን የሚንከባከቡ ከሆነና በራሳቸዉ የጥርስና የድድ ጤንነታቸዉን መጠበቅ የማይችሉ ከሆነ ይህን እንዲያደርጉ ያግዟቸዉ።



Share with: