የማጅራት ገትር በሽታን የሚያስከትሉ ተህዋሲያን ኢንፌክሸኑ ካለባቸዉ ሰዎች ከመተንፈሻ ወይም በጉሮሮ ዉስጥ ከሚነሱ ፈሳሽ ጠብታዎች ወይም ቅንጣቶች አማካኝነት ከሰው ወደ ሰው ይተላለፋሉ። እንደ መሳሳም፣ መስነጠስና አፍና አፍንጫን ሳይሽፍኑ ሰዉ ላይ ማሳል ወይም በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር በቅርብ መኖር ያሉ በጣም ቅርብርብና የተራዘመ ግንኙነት - መኖር የበሽታውን ስርጭት ይበልጥ እንዲጨምር ያደርጋል። አንድ ሰዉ የማጅራት ገትር ሊያመጡ በሚችሉ ተዋሲያን ከተያዘ በኃላ የበሽታዉን ምልክት ለማሳየት አማካይ 4 ቀናት የሚወስድ ቢሆንም ህመሙ አንድ ሰዉ ለኢንፌክሸን ከተጋለጥ በኃላ የህምመም ምልክቶቹ በአጠቃላይ ከ 2 እስከ 10 ቀናት ዉስጥ ሊያሳይ ይችላል። ባክቴሪያዉን በሰዎች ጉሮሮ ዉስጥ ሊቆይ ቢችልም የሰዎችን የበሽታ መከላከል አቅምን በማሸነፍ ወደ ደም ዉስጥ በመግባት ወደአንጎል ይሰራጫል።
ለማጅራት ገትር በሽታ አጋላጭ ነገሮች
· እድሜ፥- በቫይረስ ምክንያት የሚከሰት ማጅራት ገትር በአብዛኛዉ የሚከሰተዉ ዕድሜያቸዉ ከ 5 ዓምታት በታች ያሉ ህፃናት ላይ ሲሆን በባክቴሪያ ምክንያት የሚከሰተዉ ደግም እድሜያቸዉ ከ20 ዓመት በታች ባሉ ሰዎች ላይ ነዉ
· ክትባትን ሳይወስዱ መቅረት፥- የሚመከረዉን የልጅነት ወይም የአዋቂ ክትባት መርሃ ግብር ላልጨረሰ ሁሉ አደጋው ከፍ ይላል
· እርግዝና፥- እርግዝና በሊስትሪያ ባክቴሪያ ምክንያት የሚመጣ ኢንፌክሽን አደጋ ይጨምራል - ይህ ደግሞ የማጅራት ገትር በሽታ ሊያስከትል ይችላል።
· የበሽታ መከላከል አቅም መቀነስ፦ ኤች አይቪ ኤድስ ፣ የአልኮል ሱሰኝነት ፣ የስኳር በሽታ ፣ የበሽታ መከላከያ አቅምን የሚቀንሱ መድሃኒቶች መጠቀምና በሽታን የመከላከል ስርዓትዎ ላይ ተጽዕኖ የሚያሳድሩ ሌሎች ነገሮች እንዲሁ ለማጅራት ገትር ተጋላጭ ያደርጉዎታል።
· በአንድ አካባቢ ወይም ቦታ የተሰባሰቡ ሰዎች መኖር፦ በዶርም የሚኖሩ የኮሌጅ ተማሪዎች፣ ወታደሮች፣በቦርዲንግ ት/ቤት የሚማሩ ተማሪዎችና ሌሎችም ለሜኒንጆ ሜንጃይትስ የማጅራት ገትር አይነት ይበልጥ ተጋላጭ ናቸዉ
የጎንዮሽ ችግር ወይም ጉዳት
የማጅራት ገትር በሽታ የሚያመጣዉ የጎንዮሽ ጉዳት ውስብስብና ከፍተኛ ሊሆን ይችላል። እርስዎ ወይም ልጅዎ ህመሙ እያለ ብዙ ግዜ ከቆዩ ወይም ካሳለፉ የሚጠል በሽታና የቋሚ የነርቭ ጉዳት የመያዝ እድሉ ይጨምራል። እነርሱም
· የፀጉር መሳሳት
· የማስታወስ ችግር
· የመማር ችግር
· የአዕምሮ መጎዳት
· የአረማመድ ችግር
· የሚጠል በሽታ
· የኩላሊት መድከም
· የግፊት ከመጠን ከመጠን በላይ መቀነስ ( ሾክ)
· ለህልፈት ህይወት መዳረግና የመሳሰሉት ናቸዉ።
በማጅራት ገትር በሽታ የታመሙ ሰዎች በአስቸኳይ ህክምና ካገኙ ከባድ የማጅራት ገትር በሽታ ያለባቸው እንኳን ቢሆኑ በጥሩ ሁኔታ ሊያገግሙ ይችላሉ።