094 046 4646/0940 565656    
info@sainturaelclinic.com
Follow Us:

View Blog

የተቅማጥ በሽታ

ክፍል አንድ

አንድ ሰዉ በቀን ዉስጥ ሦስት ወይም ከዚያ በላይ ልል ወይም ፈሳሽ (ዉሃማ) ሰገራ የሚወጣ ከሆነ አሊያም ግለሰቡ ከተለመደው በላይ በተደጋጋሚ ወደመፀዳጃ ቤት የሚመላለስ ከሆነ የተቅማጥ ህመም መኖሩን ያመለክታል። ልል ወይም ዉሃማ ያልሆነና የተለመደ አይነት  ሰገራን በተደጋጋሚ መዉጣት ተቅማጥ አይደለም ፣ ወይም ደግሞ የጡት ወተት በሚጠቡ ሕፃናት ልል ሰገራ መዉጣትም ተቅማጥ አይደለም።

የተቅማጥ በሽታ ከአምስት ዓመት በታች በሆኑ ሕፃናት ላይ ሁለተኛው የሞት መንስኤ ነው። የተቅማጥ በሽታ ከአምስት ዓመት በታች በሆኑ ሕፃናት ላይ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት አንዲከሰት ከሚያደርጉ ነገሮች ዉስጥ ዋነኛ መንስኤ ነው። የተቅማጥ በሽታ መከላከልም ሆነ መታከም የሚችል ነው። ይህም ደህንነቱ የተጠበቀ ንፁህ ዉሃ በመጠጣት፣ የግልና የአካባቢን ንፅህና በመጠበቅ የሚከወን ነዉ።

የህመም ምልክቶች

·         የሆድ ቁርጠት ወይም ህመም

·         የሆድ መነፋት

·         ማቅለሽለሽ

·         ትኩሳት

·         ከሰገራ ጋር ደም መታየት

·         ንፍጥ የመሰል ነገር ከሰገራ ጋር መታየት

·         በአፋጣኝ ወደ መፅዳጃ ቤት እንዲሄዱ ተደጋጋሚ ስሜት መኖር

መንስዔዎች

በርከት ያሉ ህመሞችና ሁኔታዎች ተቅመጥ እንዲከሰት ያደርጋሉ። እነርሱም

·         ቫይረሶች፦ ተቅማጥ እንዲከሰት የሚያደርጉ ብዙ ቫይረሶች ያሉ ሲሆን ከነዚህም ዉስጥ ሮታ ቫይረስ፣ አዴኖ ቫይረስ ፣ሳይቶሜጋሎ ቫይረስና ኮሮና ቫይረሶች ይጠቀሳሉ።

·         ባክቴሪያና ፓራሳይቶች፦ ከባክቴሪያዎች እንደ ኢኮላይ ፣ ሺጌላ፣ ሳልሞኔላ እንዲሁም ከፓራሳይቶች እንደ አሜባና ጃርዲያ ያሉት በተበከለ ዉሃና ምግብ አማካኝነት ተቅማጥ እንዲከሰት ያደርጋሉ።

·         መድሃኒቶች፦ ፀረ-ባክቴሪያን ጨምሮ በዙ መድሃኒቶች ተቅማጥ እንዲከሰት ያደርጋሉ።

·         የላክቶስ አለመስማማት (Lactose intolerance) ፦ላክቶስ በወተትና ሌሎች የወተት ተዋፅኦዎች ዉስጥ የሚገኝ የስኳር አይነት ነዉ። የላክቶስ መፈጨት ችግር ያለባቸው ሰዎች የወተት ተዋጽኦዎችን ከተመገቡ በኋላ ተቅማጥ ያጋጥማቸዋል። የላክቶስ አለመስማማት ዕድሜ ሲጨምር ሊጨምር ይችላል ምክንያቱም በዕድሜዎ እየገፉ ሲሄዱ ላክቶስን ለመፍጨት የሚረዳዉ ኢንዛየም መጠን እየቀነሰ ይሄዳል።

·         ፍሩክቶስ፦ ፍሩክቶስ በተፈጥሮ በፍራፍሬዎችና ማር ዉስጥ የሚገኝ የስኳር አይነት ሲሆን በተወሰኑ መጠጦች ላይ ለማጣፈጫነት ይጨመራል። ፍሩክቶስ ያለባችዉን ምግብ መፍጨት ችግር ባጋጠማቸው ሰዎች ላይ ፍሩክቶስ ወደ ተቅማጥ ሊያመራ ይችላል

·         ሰዉሰራሽ ማጣፈጫዎች፦ ሶርቢቶል ፣ ኤሪትሪቶል እና ማንኒቶል ሰው ሰራሽ ማጣፋጫዎች ሲሆኑ በማስቲካና በሌሎች ከስኳር ነፃ በሆኑ ምርቶች ውስጥ የሚገኝና ከአንጀት ወደ ሰዉነታችን የማይመጠጥ ሲሆን በአንዳንድ ጤናማ ሰዎች ላይ ተቅማጥ ሊያስከትል ይችላል

·         ቀዶጥገና፦ ከፊል የአንጀት ወይም የሐሞት ከረጢት ለማስወጣት የሚደረጉ ቀዶ ጥገናዎች አንዳንድ ጊዜ ተቅማጥ ሊያስከትሉ ይችላሉ

·         ሌሎች የአንጀት ችግሮች፦ እንደ አይቢኤስ፣ ክሮንስ ዲዚዝ፣ አልስሬቲቭ ኮላይቲስ፣ ሲሊያክ ዲዚዝን፡ ማይክሮስኮፒክ ኮላይትስና የትንሹ አንጀት ባክቴሪያ ከመጠን በላይ መራባት ሥር የሰደደ ተቅማጥ መከሰት ምክንያቶች ሊሆን ይችላል።


Share with: