094 046 4646/0940 565656    
info@sainturaelclinic.com
Follow Us:

View Blog

የሚያመጣዉ የጎንዮሽ ጉዳት

ክፍል ሁለት

ተቅማጥ የሰዉነትን የፈሳሽ መጣኔ በመቀነስ የሰዉነት ድርቀት ወይም ፈሳሽ መሟጠጥ( ዲሃይድሬሽን) እንዲከሰት ስለሚያደርግ ለህይወት አስጊ ነዉ። ይህ የፈሳሽ እጥረት በተለይ በህፃናት፣ በአረጋዉያንና በሽታ የመከላከል አቅማቸው በተዳከመ ሰዎች ላይ አደገኛ ነው።

የፈሳሽ እጥረት መኖሩን የሚያሳዩ ምልክቶች

·         ከመጠን በላይ የዉሃ ጥማት

·         የአፍ ወይም ቆዳ ድርቀት

·         ትንሽ ወይም ምንም ሽንት አለመዉጣት

·         የድካም፣ የማዞርና የራስምታት ስሜት መኖር

·         የጠቆረ ሽንት መኖር

በጨቅላና  በትናንሽ ሕፃናት ላይ የሰዉነት ፈሳሽ መሟጠጥ ምልክቶች

·         በሶስት ወይም ከዚያ በላይ ሰዓታት ውስጥ የሽንት ጨርቃቸዉ ወይም ዳይፐር እርጥብ  አለመኖሩ

·         የምላስና አፍ ድርቀት

·         ተኩሳት

·         ሲያለቅሱ እምባ አለመኖር

·         ድብታና መነጫነጭ መታየት

·         የአይን የጉንጭና ሆድ መሰርጎድ ናቸዉ።

ተቅማጥን መከላከል

በኢንፌክሽን ምክንያት የሚመጣን ተቅማጥ መከላከል

ተላላፊ የሆነ ተቅማጥ እንዳይዛመት እጆችዎን ይታጠቡ። በቂ የእጅ መታጠብን ለማረጋገጥ

·        በተደጋጋሚ ይታጠቡ፦ ምግብ ከማዘጋጀትዎ በፊትና ካዘጋጁ በኃላ እጅዎን ይታጠቡ። ያልበሰለ ስጋን ፣ ሽንት ቤቱን ከተጠቀሙ ፣ ዳይፐሮችን ከቀየሩ ፣ ሲያስነጥሱ ፣ ሲያስሉ እና አፍንጫዎን ከተነፉ በኋላ እጅዎን ይታጠቡ።

·         ቢያንስ ለ 20 ሰከንዶች በሳሙና  እጅዎን ይሹ፦ በእጆችዎ ላይ ሳሙና ካደረጉ በኋላ ቢያንስ ለ20 ሰከንዶች ያህል እጆችዎን ይሹ።

·         እጅዎን በዉሃና ሳሙና መታጠብ በማይቻልበት ጊዜ የእጅ ማጽጃ ( ሳንታዘር ) በመጠቀም እጅዎን ያፅዱ።

በተጨማሪም

·         ክትባት መዉሰድ፦ ይህም እንደ ሮታ ቫይረስ ያሉ ተቅማጥ አምጪዎችን ለመከላከል ይረዳል

·         የንፁህ የመጠጥ ውሃ ተደራሽነትን መጨመር

·         የግልና የምግብ ንፅህናን መጠበቅ

·         ለመጀመሪያዎቹ ስድስት ወራት ህፃናትን ጡትና ጡት ብቻ መመግብ ናቸዉ።

ተቅማጥን ለማከም ቁልፍ እርምጃዎች የሚከተሉትን ያካትታሉ

·         ፈሳሽ ማጠጣት - ለዚህም ኦአርኤስ (ORS) ተመራጭ ነዉ ፣  ኦአርኤስ የንፁህ ዉሃ፣ የጨውና የስኳር ድብልቅ ነው። ኦአርኤስ ከትናንሹ አንጀት ውስጥ የሚመጠጥና ሰዉነታችን በተቅማጡ ምክንያት ያጣዉን  ውሃና ንጥረ-ነገሮች(ኤሌክትሮላይቶች) ለመተካት ያገለግላል።

·         ዚንክን በተጨማሪነት መጠቀም፦ ዚንክ የተቅማጥን እርዝማኔ ይቀንሳል መጠኑንንም ይቀንሳል

·         የፈሳሽ እጥረቱ ከፍተኛ ከሆነ በደም ስር ግሉኮስ መዉሰድ

·         የምግብ ይዘታቸዉ ከፍተኛ የሆኑ ምግቦችን መመገብ፦ ከተቅማጥ ጋር ተያይዞ የሚመጣዉን የምግብ ዕጥረት ለመከላከል የምግብ ይዘታቸዉ ጥሩ የሆኑ ምግቦችን መመገብ፣ ይህ ጡት ማጥባትን ይጨምራል። ከስድስት ወር በታች የሆኑ ህፃናት ከመድሃኒት በስተቀር ጡትና ጡት ብቻ መመገብ ያስፈልጋል

·         የማያቋርጥ ተቅማጥ ፣ የፈሳሽ ዕጥረት ምልክቶች ካሉና ደም ከትቅማጥ ጋር ካሉ የጤና ባለሙያ ማማከር ያስፈልጋል።

Share with: