ክፍል አንድ
የትንፋሽ ማጠር አለዎት? የትንፋሽ ማጠር ካለዎና በተለይ በድንገት የተከሰት ከሆነ ከልብ ወይም ከሳንባ ችግር ምክንያት ሊከሰት ስለሚችል በኣስቸኳይ የህክምና ባልሙያዎን የማክሩ
አብዛኛው የትንፋሽ እጥረት የሚከሰተዉ በልብ ወይም በሳንባ ችግር ምክንያት ነው ። ልብዎ እና ሳንባዎ ኦክስጅንን ወደ ሰዉነት ክፍሎች (ቲሹዎችዎ) በማጓጓዝና ካርቦን ዳይኦክሳይድን በማስወገድ ይሳተፋሉ። ከእነዚህ ከሁለቱ የአንዱ አካል መጎዳት አተነፋፈስዎ ላይ ችግሮች እንዲከሰቱ ያደርጋል።
በድንገት የሚመጣ የትንፋሽ እጥረት (አጣዳፊ የትንፋሽ ዕጥራት ይባላል) የተወሰኑ ምክንያቶች አሉት። ከነዚህም ምክንያቶች ዉስጥ
· አስም
· በካርቦን ሞኖ ኦክሳይድ ጭስ መመረዝ
· ከባድ የአለርጂ ምላሽ (አናፍላክሲስ)
· በልብ ሽፋን ዙርያ ፈሳሽ በብዛት መጠራቀም
· የኮቪድ 19 ህመም
· ድንገታዊ የልብ ችግር (Heart attack)
· የልብ ምት መዛባት (የልብ ምት ችግሮች)
· የልብ ድካም
· የሳንባ ምች
· የአየር ካሳንባ ዉጪ ምፍሳስ( ኒሞቶራክስ)
· የሳንባ ደም ቅዳ መዘጋት ( ፑልሞናሪ ኢንቦሊዝም)
· ድንገታዊ የደም መፍሰስ
· የላይኛው የመተንፈሻ ቱቦ መዘጋት (የአየር መተላለፊያ መዘጋት)
ለሳምንታት ወይም ከዚያ በላይ የቆየ የትንፋሽ እጥረት ወይም ስር የሰደደ የትንፋሽ ማጠር ችግር መኖር በሚከተሉት ምክንያቶች ሊከሰት ይችላል
· አስም
· ስር የሰደደ የሳንባ የአየር ቧንቧ መዘጋት ችግር ( ሲኦፕዲ)
· የልብ ድካም
· ከመጠን ያለፈ ዉፍረት
· የሳንባ ዉሃ መቋጠር
· የደም ማነስ
· የሳንባ ቲቢና የመሳሰሉት ናቸዉ።