ማቅለሽለሽ የሆድ ምቾት ማጣትና ማስታወክ የመፈለግ ስሜት ነው። ማቅለሽለሽ አንድ ሰዉ ከማስታወኩ በፊት የሚከሰት የህመም ምልክት ሊሆን ይችላል። ሁኔታው ብዙ ምክንያቶች አሉት ፤ እንዲሁም መከላከል ይቻላል።
የማቅለሽለሽ መንስኤ ምንድነው
ማቅለሽለሽ ብዙ መንስዔዎች አሉት ። መቅለሽለሽ እንዲከሰት ከሚያደርጉ ዉስጥ
· ቃር ወይም ጋስትሮኢሶፋጂያል ሪፍሌክስ ዲዚዝ፦ ይህ በጨጓራዎ ዉስጥ ያለዉ እየተፈጨ ያለዉ ምግብ ወደ ምግብ መተላለፊያ ቱቦ በሚመለስበት ወቅት የሚከሰት ነዉ። ይህ የማቅለሽለሽ ስሜትን የሚያስከትል የማቃጠል ስሜት ይፈጥራል።
· ኢንፌክሽን፦ በባክቴሪያ ወይም በቫይረሶች ኢንፌክሽን በጨጓራዎ ላይ ሲፈጠር የማቅለሽለሽ ስሜት እንዲፈጠር ሊያደርግ ይችላል።።በሆድ ላይ ተጽዕኖ ሊያሳድሩ እና ወደ ማቅለሽለሽ ሊያመሩ ይችላሉ። ምግብ ወለድ የባክቴሪያ ኢንፌክሽኝ የምግብ መመረዝ በመባል የሚታወቅ በሽታ ሊያስከትል ይችላል። የቫይረስ ኢንፌክሽኖች ማቅለሽለሽ ሊያስከትሉ ይችላሉ።
· መድሃኒቶች፦ በህክምና ባልሙያዎ የሚታዘዙ መድሃኒቶች ማቅለሽለሽ ሊያስከትሉ ይችላሉ።
· በትራንስፖርት ላይ ሲጓጓዙ ፦ በተሽከርካሪ ላይ ከአስቸጋሪ ጉዞ የተነሳ ሊመጣ ይችላል።
· አመጋገብ፦ ከመተጠን በላይ መመገብ አሊያም ቅመምና ቅባት የበዛባቸዉ ምግቦችና አለርጂ የሆኑባቸዉን ምግቦችን መመገብና የጨጓራ መታወክ ሊያመጣ ስለሚችል ማቅለሽለሽ ሊያስከትል ይችላል።
· ህመም፦ ኃይለኛ ህመም ለማቅለሽለሽ ምልክቶች አስተዋፅኦ ሊያደርግ ይችላል። ይህ እንደ የቆሽት መቆጣት ( ፓንክሪታይቲስ) ፣ የሀሞት ጠጠር፣ ወይም የኩላሊት ጠጠር ከፍተና ህመም ሊያምጡ የሚችሉ ችግሮች ማቅለሽለሽ ሊያመጡ ይችላሉ።
· ቁስለት፦ የጨጓራና የትንሹ አንጀት የዉስጠኘዉ ሽፋን ቁስለት ለማቅለሽለሽ አስተዋፅኦ ያደርጋሉ
መቅለሽለሽ ለሚከተሉት ህመሞች የህመም ምልክት ሊሆን ይችላል
· የጆሮ ኢንፌክሽን
· የድንገተኛ ልብ ህመም
· የአንጀት መታጠፍ
· የጉበት መድከም
· የጉበት ካንሰር
· የማጅራት ገትር
· የምይግሬይን የራስ ምታትና የመሳስሉት ናቸዉ።