አኩሪ አተር ከአበባ እህሎች ዉስጥ የሚመደብ ሲሆን ለምግብነት በተለያየ መልክ ይዉላል። አኩሪ አተር ብዙውን ጊዜ ሳይቀነባበር አንዳለ መመገብ ይቻላለ አሊያም በተለያየ አይነት ተቀነባብሮ ለምግብነት ሊዉል ይችላል። የአኩሪ አተር ዱቄት ፣ የአኩሪ አተር ፕሮቲን ፣ ቶፉ ፣ የአኩሪ አተር ወተት ፣ የአኩሪ አተር ሶስና የአኩሪ አተር ዘይት ጨምሮ የተለያዩ የአኩሪ አተር ምርቶች ይገኛሉ።
የአኩሪ አተር የምግብ ይዘቶች
አኩሪ አተር በዋናነት በፕሮቲን የበለፀገ ሲሆን ካርቦሀይድሬትና ስብንም በጥሩ መጠን ይዟል።
ፕሮቲን
አኩሪ አተር ከዕፅዋት ከሚገኝ ፕሮቲን ምርጥ ምንጮች ውስጥ ዋነኛዉ ነዉ። የአኩሪ አተር የፕሮቲን ይዘት ከደረቅ ክብደት 36-56% ይይዛል። ከተቀቀለ 172 ግራም አኩሪ አተር 29 ግራም ፕሮቲን (ገንቢ ምግብ) እናገኛለን። የአኩሪ አተር ፕሮቲንን መመገብ የሰዉነት ስብ መጠንን በተወሰን መጠን ለመቀነስ ይረዳል።
ስብ
አኩሪ አተር እንደ የቅባት እህሎች ተመድቦ የአኩሪ አተር ዘይት ለመሥራት ያገለግላል። የስብ ይዘቱ ከደረቅ ክብደት በግምት 18% ነው (ስቡ ጤነኛ ስብ ሲሆን በአብዛኛዉ ፖሊሳቹሬትድና ሞኖሳቹሬትድ የስብ አይነቶች ናቸዉ፤ አኩሪ አተር በመጠኑም ቢሆን ጤነኛ ያልሆነ ወይም ሳቹሬትድ ስብ ይዟል)።
ሀይል ሰጪ ( ካርቦሀይድሬትስ)
አኩሪ አተር በጣም አነስተኛ የሆነ ሀይልሰጪ ( ካርቦሃይድሬት) መጠን የያዘ ስለሆነ አኩሪ አተርን የስኳር በሽታ ባላቸው ሰዎች ላይ ተስማሚ ወይም ተመራጭ ያደርገዋል።
ፋይበር
አኩሪ አተር ሁለቱንም ማለትም የሚሟሟና የማይሟሟ ፋይበር የያዘ ነዉ። ፋይበር በትልቁ አንጀት ዉስጥ ባሉ ባክቴሪያዎች በመብላላት ወደ አጭር ሰንሰለታማ ስቦች (SCFAs) ይቀይሩታል። ይህም የአንጀት ጤናን ለማሻሽልና በአንጀት ካንሰር የመያዝ እድልን ለመቀነስ ይረዳል።
ቫይታሚንና ማዕድን
አኩሪ አተር የቫይታሚንና የመዕድናት ጥሩ ምንጭ ሲሆን ከነዚህም ዉስጥ
· ቫይታሚን ኬ፦
· ፎሌት
· ኮፐር( መዳብ)
· ማንጋኔዝ
· ፎስፎረስ
· ቲያሚን
· ሞልብድኒያም ይይዛል።
የአኩሪ አተር የተወሰኑ የጤና ጥቅሞች
· የካንሰር ተጋላጭነትን ይቀንሳል፦ አኩሪ አተር የጡት፣ የፕሮስቴትና የአንጀት ካንሰሮች ተጋላጭነትን ይቀንሳል
· ከወር አበባ ማራጥ ጋር ተያይዞ የሚመጡ የህመም ምልክቶችን ለመቀነስ ይረዳል
· ለአጥንት ጤንነት፦ የአኩሪ አተር ምርቶችን መጠቀሙ ባረጡ ሴቶች ላይ የአጥንት መሳሳትን አደጋ ሊቀንስ ይችላል