094 046 4646/0940 565656    
info@sainturaelclinic.com
Follow Us:

View Blog

የጡት ካንሰር

ክፍል አንድ 


የጡት ካንሰር በጡት ሕዋሳት ውስጥ የሚፈጠር ካንሰር ነው በሌላ አነጋገር የጡት ካንሰር በጡት ውስጥ ያሉ ሕዋሳት ከቁጥጥር ውጭ ሆነው በሚያድጉበት ወቅት የሚመጣ በሽታ ነው። የጡት ካንሰር በወንዶችም በሴቶችም ላይ የሚከሰት ቢሆንም  በሴቶች ላይ ግን  በጣም የተለመደ ነው።

የህመም ምልክቶች

·         ከአካባቢው ሕብረ ሕዋስ የተለየ ስሜት ያለዉ የጡትና ብብት ስር  እብጠት ወይም ውፍረት መከሰት

·         የጡት መጠን ፣ ቅርፅ ወይም ገጽታ መለወጥ

·         የጡት የሆነ ክፍል ውፍረት ወይም እብጠት መኖር

·         ከእናት ጡት ወተት በስተቀር ደምን ጨምሮ ከጡት ጫፎች ፈሳሽ መከሰት።

·         በቅርቡ የተከሰተ የጡት ጫፍ ወደዉስጥ መግባት ወይም መገልበጥ

·         በጡት ጫፍ ዙሪያ ያለዉ ጥቁሩ ቆዳ ወይም የጡት ቆዳ መፋፋቅና ማበጥ

·         የጡትዎ ቆዳ  መቅላት ወይም እንደብርቲካን ቆዳ የመሰለ የጡት ቆዳ ላይ ጠቃጠቆ መሆን ዋና ዋናዎቹ ናቸዉ።

ለጡት ካንሰር አጋላጭ ነገሮች

ጥናቶች እንደሚያሳዩት ለጡት ካንሰር የመጋለጥ እድልዎ የሚጨምሩት የተዋሃዱ ምክንያቶች ነው። ለችግሩ መከሰት ተጽዕኖ የሚያሳድሩ ዋና ዋና ምክንያቶች ሴት መሆንና በዕድሜ መግፋት ወይም እርጅና ናቸዉ ። አብዛኛዎቹ የጡት ካንሰሮች የሚከሰቱት ዕድሜያቸው 50ና ከዚያ በላይ በሆኑ ሴቶች ላይ ነው።

አንዳንድ ሴቶች የሚታወቁ ለጡት ካንሰር አጋላጭ ምክንያቶች ወይም ሌሎች ሁኔታዎች ሳይኖሩባቸው በጡት ካንሰር ይያዛሉ። ለጡት ካንሰር አጋላጭ ምክንያቶች አለዎት ማለት በሽታ ይያዛሉ ማለት ግን አይደለም ፤ እንዲሁም ሁሉም አጋላጭ  ምክንያቶች ተመሳሳይ ውጤት ይኖራቸዋል ማለትም አይደለም። አብዛኛዎቹ ሴቶች የተወሰኑ ለጡት ካንሰር አጋላጭ ምክንያቶች አሏቸው ፣ ነገር ግን አብዛኛዎቹ ሴቶች በጡት ካንሰር አይያዙም። ለጡት ካንሰር ተጋላጭነት ምክንያቶች ካሉዎት ፣ በጡት ካንሰር የመያዝ ዕድልዎን ለመቀነስ ስለሚችሉባቸው መንገዶችና የጡት ካንሰር ቅድም-ምርመራን በተመለከተ ከሐኪምዎ ጋር ይወያዩ።

Share with: