094 046 4646/0940 565656    
info@sainturaelclinic.com
Follow Us:

View Blog

የኮቪድ 19 (COVID-19) የረጅም ጊዜ ችግሮች

ምንም እንኳን በኮቪድ (COVID) 19 የተያዙ አብዛኛዎቹ ሰዎች የሚያገግሙና ወደ መደበኛው ጤናቸዉ የሚመለሱ ቢሆንም አንዳንድ ሕመምተኞች ከከባድ በሽታ ካገገሙ በኋላ ለሳምንታት ወይም ለወራት የሚቆዩ ምልክቶች ሊኖራቸው ይችላል፡፡ ሆስፒታል ያልገቡ እና ቀላል ህመም ያላቸው ሰዎች እንኳን ቢሆኑ ረጅም ጊዜ የሚቆይ አሊያም የረዘመ የህመም ምልክቶች ሊታዩባቸዉ ይችላሉ፡፡ አነዚህ ምልክቶች በምን ያህል መጠን እንደሚከሰቱ፣ በነማን ላይ እንደሚፀናና መቼ ሙሉ በሙሉ ይጠፋሉ የሙሉትን ነገሮች ለማወቅ ጥናቶች እንደቀጠሉ ናቸዉ፡፡
በብዛት ሪፓርት ተደረጉ ለረጅም ጊዜ ሊቆዩ ወይም ሊታዩ ከሚችሉ ምልክቶች ዉስጥ የሚከተሉት ይጠቀሳሉ፡፡
•ድካም
•የትንፋሽ ማጠር
•ሳል
•የመገጣጠሚያ ላይ ህመም
•የደረት ህመም በብዛት ተመዘገቡ ሲሆን
ሌሎች ሪፖርት የተደረጉ ደግሞ
•የአስተሳሰብ እና የትኩረት ችግር መፈጠር (አንዳንድ ጊዜ “የአንጎል ጭጋግ” ይባላል)
•ድብርት
•የጡንቻ ላይ ህመም
•የራስ ምታት
•አለፍ ገደም እያለ የሚመጣ የሰዉነት ትኩሳት እንዲሁም
•የልብ ትርታ መጨመር ናቸዉ፡፡
በጣም ከባድ የረጅም ጊዜ ችግሮች ብዙም ያልተለመዱ ቢሆንም ነገር ግን ሪፖርት ተደርገዋል፡፡ የእነዚህ የረጅም ጊዜ ችግሮች ተፅእኖ ወይም የወደፊት የጤና ተግዳሮት እስከምን ደረጃ ነዉ የሚለዉ ያልታወቀ ሲሆን በጥናት ላይ ይገኛል፡፡ እነዚህ በሰውነታችን ውስጥ በተለያዩ የአካል ክፍሎች ላይ የሚያሳድሩት ተጽዕኖ ግን ታዉቛል፡፡ እነዚህም፡-
•የልብና የደም ቧንቧ ችግር፡- የልብ ጡንቻ መቆጣት
•የመተንፈሻ አካል፡- የሳንባ ተግባራት ላይ ያልተለመዱ ነገሮች መከሰት
•ኩላሊት፡- ድንገተኛ የኩላሊት ጉዳት
•ቆዳ፡- ሽፍታ፣ የፀጉር መርገፍ
•የነርቭ ስርዓት፡- የማሽተትና የመቅመስ ችግሮች፣ የእንቅልፍ ችግር፣ የትኩረት ችግር፣ የማስታወስ ችግሮች
•የስነአዕምሮ፡- ድብርት፣ የስሜት መለዋወጥ፣ መጨናነቅ ናቸዉ፡፡
ማስታወሻ ፡- እነዚህን የረጅም ጊዜ ችግሮች ለመከላከል ከሁሉ የተሻለው መንገድ ኮቪድን (COVID-19) መከላከል ነው ፡፡ በወጣቶች እና በጎልማሶች ላይ የኮቪድ 19 (COVID-19) ኢንፌክሽንን ለመከላከል በጣም ጥሩ ወይም ዉጤታማ መንገዶች በሕዝብ ቦታዎች ላይ የፊትና አፍንጫ ጭምብል ማድረግ ፣ ከሌሎች ሰዎች ቢያንስ ከ 6 ፊት ወይም የ2 ሜትር ርቀት መጠበቅ ፣ እጅዎን አዘውትረው መታጠብ እና ብዙ ሰዎች የተሰበሰቡበት እንዲሁም አየር በደንብ በማይዘዋወርበት ወይም ከታፋፈጉ ቦታዎች መቆጠብ/አለመቆየት ወይም ከነዚህ ቦታዎች መራቅ ናቸዉ፡፡

Share with: