ክፍል ሁለት
ታይፈስ ሊያመጣዉ የሚችላዉ የጎንዮሽ ጉዳት
ካልታከሙት ታይፈስ ከባድ እና አልፎ ተርፎም ለህይወት አስጊ የሆኑ ችግሮችን ሊያስከትል ይችላል። እነሱም የሚከተሉትን ያካትታሉ:-
· የአንጎልና የህብለሰረሰር መቆጣትና እብጠት
· የጣፊያ እብጠት
· የልብ ጡንቻና ቫልቮች መቆጣት
· የዉስጥ አካል መድማት
· የኩላሊት መጎዳት
· የጉባት መጎዳት
· የደም ግፊትን መቀነስ
· የሳንባ ምች
· ሴፕቲክ ሾክ
ታይፈስን መከላከል
ታይፈስን ለመከላከል የሚያስችል ምንም ክትባት የለም። ነገር ግን ታይፈስን ለመከላከል የሚያስችል እርምጃዎችን መተግበር ያስፈልጋል።
የታይፈስ ህክምና
ታይፈስ በፀረ-ባክቴሪያ መድሃኒቶቸ የሚታከም ሲሆን ሊሰጡ ከሚችሉ መድሃኒቶች ዉስጥ ዶክሲሳይክሊንና ክሎራምፌኒኮልን ሊያካትት ይችላል። የታይፈስ የህመም ምልክቶች ካለዎ የህክምና ባልሙያዎን ያማክሩ።