094 046 4646/0940 565656    
info@sainturaelclinic.com
Follow Us:

View Blog

የጆሮ ኢንፌክሽን (otitis media)

የጆሮ ኢንፌክሽን (አንዳንድ ጊዜ አጣዳፊ የመካከለኛዉ ጆሮ ኢንፌክሽን ወይም  otitis media ተብሎ የሚጠራው) የመሃከለኛ ጆሮ ክፍል ኢንፌክሽን ነው። መካከለኛዉ የጆሮ ክፍል ከጆሮው ታምቡር በስተጀርባ በአየር የተሞላው ክፍት ክፍል ሲሆን  የጆሮን ጥቃቅን የሚንቀጠቀጡ አጥንቶች የያዘ ነዉ። ልጆች ከአዋቂዎች በበለጠ ለጆሮ ኢንፌክሽን የተጋለጡ ናቸዉ።

የጆሮ ኢንፌክሽኖች ብዙ ጊዜ በራሳቸው ስለሚጠፉ ወይም ስለሚድኑ ህክምናው ህመሙን በመቆጣጠርና ችግሩን በመከታተል ሊጀምር ይችላል።

አንዳንድ ጊዜ ኢንፌክሽኑን ለማከም ፀረ- ባክቴሪያ መድሃኒቶች ሊታዘዙ ይችላሉ። አንዳንድ ሰዎች ለተደጋጋሚ የጆሮ ኢንፌካሽን የተጋላጡ ሊሆኑ ይችላሉ። ይህም የመስማት ችግርና ሌሎች ከባድ የጎንዮሽ ችግሮችን ሊያስከትል ይችላል።

የህመም ምልክቶች

የጆሮ ኢንፌክሽን ምልክቶች ለመታየት  ብዙውን ጊዜ ፈጣን ናቸዉ።ምልክቶቹም

·         የጆሮ ህመም-- በተለይ ጋደም ሲሉ

·         ጆሮ ላይ የመጎተት ስሜት መከሰት

·         እንቅልፍ መንሳት

·         ለህፃናት ከወትሮዉ በተለየ ሁኔታ ማልቀስ

·         ለመስማት መቸገር ወይም ለድምጾች ምላሽ መስጠት ላይ መቸገር

·         ባላንስ ማጣት

·         ከጆሮ ፈሳሽ መኖር

·         የሰዉነት ትኩሳት በተለይ ለልጆች

·         የራስ ምታት

·         የምግብ ፍላጎት ማጣት ናቸዉ።

አጋላጭ ነገሮች

·         እድሜ፦ ከ 6 ወር እስከ 2 አመት እድሜ ያላቸው ልጆች ለጆሮ ኢንፌክሽን በጣም የተጋለጡ ናቸው

·         የልጆች ያጋራ እንክብካቤ( ለምሳሌ ህፃናት እንክብካቤ ማዕከል)፦

·         የህፃናት አመጋገብ፦ ጡጦ የሚጠቡ ሕፃናት (በተለይም ተኝተው ) ጡት ከሚጠቡ ሕፃናት የበለጠ የጆሮ ኢንፌክሽን ይያዛሉ።

·         ወቅታዊ ሁኔታዎች፦ ወቅታዊ አለርጂ ያለባቸው ሰዎች የአበባ ብናኝ ብዛት ከፍተኛ በሚሆንበት ጊዜ ለጆሮ ኢንፌክሽን የመጋለጥ እድላቸው ከፍተኛ ሊሆን ይችላል።

·         አነስተኛ የአየር ጥራት፦ ለትንባሆ ጭስ መጋለጥ ወይም ከፍተኛ የአየር ብክለት ለጆሮ ኢንፌክሽን ተጋላጭነትን ይጨምራል።

·         የላንቃ መሰንጠቅ። የላንቃ መሰንጠቅ ባለባቸው ሰዎች ይበልጥ ለጆሮ ኢንፌክሽን የመጋለጥ እድላቸዉ ከፍትኛ ነዉ።


Share with: