094 046 4646/0940 565656    
info@sainturaelclinic.com
Follow Us:

View Blog

የሰዉነት የስኳር መጠን መቀነስ (Hypoglycemia)

እንደሚያዉቀት ግሉኮስ የሰውነትዎ ዋና የኃይል ምንጭ ነው። አንድ ጤነኛ ሰዉ የሰዉነት የስኳር መጠኑ በደም ዉስጥ ሲለካ በሁለት መልክ ሊገለፅ ይችላል። አንዱ በባዶ ሆድ የሚሰራዉ ሲሆን ልኬቱ ከ70 እስከ 100 ሚግ በዴሲሜትር መሆን ያለበት ሲሆን ሁለተኛዉ ምግብ ከበሉ በኋላ የሚሰራዉ ነዉ፤ የስኳር ልኬት መጠኑ ደግሞ ከ70 እስከ 140 ሚሊግራም በዴሲሜትር መሆን አለበት

በደምዎ ውስጥ ያለው የስኳር መጠን (ግሉኮስ) ከመደበኛው ያነሰ ከሆነ ( ወይም ከ70 ሚሊግ በዴሲሜትር በታች ከሆነ) የደም ስኳር መቀነስ ችግር (ሀይፖግላይሴሚያ) ይባላል።

የሰዉነት የስኳር መጠን መቀነስ አብዛኛዉን ጊዜ ከስኳር ህመም ህክምና ጋር የተያያዘ ነዉ። ይሁንና አልፎ አልፎ ከስኳር ህመም ጋር ሳይያያዝ የሰዉነት የስኳር መጠን መቀነስ ችግር ሊከሰት ይችላል። በደም ውስጥ ያለው የስኳር መጠን ዝቅተኛ ሲሆን  (ሃይፖግላይሴሚያ )አፋጣኝ ሕክምና ያስፈልገዋል። ለአብዛኛዉ ሰዎች ተፁሞ የሚሰራዉ የደም የስኳር መጠን 70 ሚሊግራም በዴሲሊተርና ወይም ከዚያ በታች ከሆነ የደም ስኳር ማነስ ችግር (ህይፖግላይሴሚያ) አለዉ ይባላል።

የህመም ምልክቶች

በደም ውስጥ ያለው የስኳር መጠን በጣም ዝቅተኛ ከሆነ የሚከተሉት የህመም ምልክቶች ሊታዩ  ይችላሉ፦

·         ድካም

·         የቆዳ መንጣት

·         መደበኛ ያልሆነ ወይም ፈጣን የልብ ምት

·         መንቀጥቀጥ

·         መጨናነቅ

·         ማላብ

·         የረሃብ ስሜት

·         መቅበጥበጥ

·         የምላስ፣ከንፈርና ጉንጭ መተሳሰር፣ መደንዘዝ

የስኳር ማነሱ እየተባባሰ ከመጣ የህመም ምልክቶቹ

·         ግራ መጋባት፣ ያልተለመደ ባህሪ መታየት ወይም ሁለቱም፤ እንዲሁም  መደበኛ ተግባራትን መከወን አለመቻል

·         የአይን ብዥ ማለት

·         እንዳሚጥለዉ ሰዉ የሰዉነት መንቀጥቀጥ

·         እራስን መሳትና የመሳሰሉት ምልክቶች ሊታዩ ይችላሉ።

የስኳር ማነስ ምልክቶች ካለዎት ወይም የስኳር ህመም ታማሚ ከሆኑና ለስኳር ማነስ ችግሩ ጅዉስ፣ ለስላሳ፣ ከረሜላ ወይም ግልኮስ እንክብሎችን ወስደሁ ያልተሻለዎ ከሆነ በአፋጣኝ የህክምና ባለሙያዎን ያማክሩ።

Share with: