094 046 4646/0940 565656    
info@sainturaelclinic.com
Follow Us:

View Blog

የሰዉነት የስኳር መጠን መቀነስ መንስዔ

ክፍል ሁለት

ሃይፖግላይሴሚያ የሚከሰተው በደምዎ ውስጥ ያለው የስኳር መጠን (ግሉኮስ) መጠን በጣም ሲቀንስ ነው። ይህ ሊከሰት የሚችልባቸው በርካታ ምክንያቶች ያሉ ቢሆንም በጣም የተለመደው ግን የስኳር በሽታን ለማከም የሚሰጡ መድሃኒቶች የጎንዮሽ ጉዳት ዉጤት ነዉ።

የስኳር ህመም ሳይኖር ለህይፖግላይሴሚያ ሊያጋልጡ የሚችሉ ነገሮች

የስኳር በሽታ በሌላቸዉ ሰዎች ላይ የደም ስኳር ማነስ ችግር (ሃይፖግላይሴሚያ ) የመከሰት እድሉ በጣም አናሳ ነው። ምክንያቶች የሚከተሉትን ሊያካትቱ ይችላሉ:

·         መድሃኒቶች፦ የስኳር መድሃኒት በስህተት ከወሰዱ፣ሌሎች ስኳርን የሚቀንሱ መድሃኒቶች የሚወስዱ ከሆነ

·         ከመጠን ያለፈ አልኮሆል መጠጠት፦ ሳይመገቡ አልኮሆል በብዛት መጠጣት በጉበትዎ ዉስጥ የተከማቸ ግሉኮስ ወደ ደምዎ ውስጥ እንዳይለቀቅ ያግዳል ይህም ሃይፖግላይሴሚያ እንዲከሰት ያደርጋል።

·         ከባድ ህመም ሲኖር፦ ከባድ የጉበትና ኩላሊት ህመሞች ለስኳር ማነስ መከሰት ምክንያት ሊሆኑ ይችላሉ።

·         የኢንሱሊን ከመጠን በላይ በሰዉነትዎ ዉስጥ መመረት፦ በቆሽትዎ ላይ ኢንሱሊን አመንጪ እጢ መኖር ከመጠን በላይ ኢንሱሊን እንዲያመነጭ ሊያደርግ ይችላል።በዚህም ምክንያት ሃይፖግላይሚያ (hypoglycemia) እንዲከሰት ያደርጋል

·         የሆርሞን እጥረት መከሰት፦ አንዳንድ የአድሬናልና የፒቱታሪ ዕጢ መዛባቶች የግሉኮስ ምርትን የሚቆጣጠሩ ቁልፍ ሆርሞኖች እጥረት ሊያስከትሉ ይችላሉ።

የስኳር ማነስ ሊያመጣ የሚችለዉ የጎንዮሽ ጉዳት

•           እንደሚጥ በሽታ ማንቀጥቀጥ

•           እራስን መሳት

•           መደካከምና ማዞር

•           መዉደቅ

•           በሚወድቁበት ወቅት አደጋ መከሰት

•           የመኪና አደጋ መከሰት

•           በአዋቂዎች ላይ ከፍተኛ የመርሳት ችግር

•           ሞት ናቸዉ።

መከላከል

የስኳር ህመም ታካሚ ከሆኑና መድሃኒት እየወሰዱ ከሆነ የስኳር መድሃኒትዎን በሀኪምዎ ትእዛዝ መሰረት ይዉሰዱ። አዲስ የስኳር መድሃኒት ከቀየሩ፣ የአመጋገብና የመድሃኒት አወሳሰድ መርሃግብርዎን ከአቀየሩ አሊያም አዲስ አይነት የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ከጀመሩ ለዉጦቹ በስኳሩ ላይ ሊያመጣ የሚችለዉን ለዉጥ ለመረዳት የህክምና ባለሙያዎን ያማክሩ።

የስኳር ህመም ታካሚ ካልሆኑና የሰዉነት የስኳር መጠንዎ በተደጋጋሚ የሚያንስ ከሆነ ትንሽ ትንሽ በተደጋጋሚ መመገብ የስኳር ማነስ ችግርን ለመቅረፍ ይረዳዎታል። ይህን አይነት አካሄድ ለረጅም ጊዜ መተግበር አስቸጋሪና የማይመከር ስለሆነ ለችግሩ ምንጭ ምን እንደሆነ ለማወቅ የህክምና ባለሙያዎን ያማክሩ።


Share with: