094 046 4646/0940 565656    
info@sainturaelclinic.com
Follow Us:

View Blog

ትኩሳት (Fever)

ትኩሳት አብዛኛውን ጊዜ በህመም ምክንያት የሰውነትዎ ሙቀት በጊዜያዊነት ሲጨምር የሚከሰት ነው። የትኩሳት መከሰት በሰውነትዎ ውስጥ ያልተለመደ ነገር እንዳለ የሚያሳይ ምልክት ነው። ተቀባይነት ያለዉ የሰዉ አማካይ መደበኛ የሰውነት ሙቀት መጠን 37°C ነዉ። የሰዉነት ሙቀት መጠን ሙሉ ቀን አንድ አይነት ሆኖ አይቆይም፣በህይወትዎ ዘመንዎ ዉስጥም  ሁሉ ይለያያል። በቀን ውስጥ የሙቀት መጠንዎ እንዲለዋወጥ የሚያደርጉ አንዳንድ ነገሮች የሚከተሉትን ያካትታሉ:

·         ምን ያህል ንቁ እንደሆኑ

·         ሙቀቱ በየትኛዉ የቀኑ ሰዓት አንደለተለካ

·         እድሜ

·         ፆታ

·         የበሉትን ወይም የሚጠጡት ነገሮች ሊወስኑት ይችላሉ።

አንድ ሰዉ ተኩሳት አለዉ የሚባለዉ ለአዋቂዎች  የአፍ ወይም የብብት ሙቀት መጠን  ከ37.6°C (99.7°F) ወይም የፊንጢጣ ወይም የጆሮ ሙቀት ከ38.1°C (100.6°F) በላይ ከሆነ ትኩሳት አለዉ ይባላል።

የህመም ምልክቶች

ትኩሳትዎን በሚያመጣው ላይ በመመስረት ተጨማሪ የትኩሳት ምልክቶች የሚከተሉትን ሊያካትቱ ይችላሉ-

·         የሰዉነት ማላብ

·         ብርድ ብርድ ማለትና ማንቀጥቀጥ

·         የራስ ምታት

·         የጡንቻ ላይ ህመም

·         የምግብ ፍላጎት ማጣት

·         መቅበጥበጥ/መነጫነች

·         የሰዉነት ፈሳሽ እጥረት

·         መደካከም ናቸዉ።

·         እድሚያቸዉ ከ5 ወር እስከ 5 ዓመት ያሉ ህፃናት ትኩሳት ሲኖራቸዉ አንደሚጥለዉ ሰዉ የሰዉነት ማንቀጥቀጥ ሊኖራቸዉ ይችላል

ከትኩሳት በተጨማሪ የሚከተሉት ምልክቶች ካለዎ የህክምና ባልሙያዎን ያማክሩ

·         ከፍተኛ የራስ ምታት

·         ያልተለመደ የቆዳ ላይ ሽፍታ

·         ያልተለመደ ብርሃን ሲያዩ የሚያስቸግርዎ ከሆነ

·         የማጅራት መገተር

·         በተደጋጋሚ ማስታወክ

·         መተንፈስ መቸገር ወይም የደረት ዉጋት

·         የሆድ ቁርጠት

·         ሽንት ሲሰኙ ህመም መኖር

·         መቀባዥር መኖር

·         እንደሚጥለዉ ሰዉ ማንቀጥቀጥ ናቸዉ



Share with: