094 046 4646/0940 565656    
info@sainturaelclinic.com
Follow Us:

View Blog

የጆሮ ኢንፌክሽን የሚያመጣዉ የጎንዮሽ ጉዳት

ክፍል ሁለት

አብዛኛዎቹ የጆሮ ኢንፌክሽኖች የረጅም ጊዜ ችግሮች አያስከትሉም። በተደጋጋሚ የሚከሰት የጆሮ ኢንፌክሽን ወደ ከባድ ችግሮች ሊመራ ይችላል:-

·         የመስማት ችሎታ ችግር፦ እየመጣ የሚሄድ ቀላል የመስማት ችግር ከጆሮ ኢንፌክሽን ጋር የተለመደ ነው። ነገርግን አብዛኛውን ጊዜ ኢንፌክሽኑ ከተወገደ በኋላ የመስማት ችግሩ ይሻሻላል። በተደጋጋሚ የሚከሰት የጆሮ ኢንፌክሽን ወይም በመሃከለኛዉ የጆሮ ክፍል ውስጥ ፈሳሽ መኖር  የበለጠ ጉልህ የሆነ የመስማት ችግር ሊያስከትል ይችላል። በጆሮ ታምቡር ወይም በሌሎች የመሃከለኛ ጆሮ ክፍል አወቃቀሮች ላይ የተወሰነ ዘላቂ ጉዳት ከደረሰ ቋሚ ወይም የማይድን የመስማት ችግር ሊያከሰት ይችላል።

·         የመናገር ወይም የእድገት መዘግየት፦ በጨቅላና ህጻናት ታዳጊዎች ላይ የመስማት ችሎታ ለጊዜው ወይም ለዘለቄታው ከተዳከመ ወይም ከቀነሰ የንግግር፣ የማህበራዊና የዕድገት ክህሎት መዘግየት ሊያጋጥማቸው ይችላል።

·         የኢንፌክሽን መዛመት፦ የጆሮ ኢንፌክሽን ኖሮ ህክምና ካላገኙ አሊያም ህክምናዉ በበቂ መጠን ካልሰራ ኢንፌክሽኑ ወደ ሌላ አካል ሊዛመት ይችላል። በዚህም ምክንያት የማጅራት ገትር፣ የጆሮ ግንድ ኢንፌክሽንና የመሳሰሉት ሊከሰቱ ይችላሉ።

·         የጆሮ ታምቡር መቀደድ፦ አብዛኛው የጆሮ ታምቡር መቀደድ በ72 ሰዓታት ውስጥ ይድናል ወይም ይጠግናል። በአንዳንድ ጊዜ ግን የጆሮ ታምቡሩን ለጠገን  የቀዶ ጥገና ሊኣስፈልግ ይችላል።

የጆሮ ኢንፌክሽንን መከላከል

የሚከተሉት ምክሮች በጆሮ ኢንፌክሽን የመያዝ እድልን ይቀንሳሉ፦

·         ጉንፋንንና ሌሎች ህመሞችን መከላከል፦ ሲያስነጥሱና ሲያስሉ በታጠፈ የዉስጠናዉ ክርን አፍንና አፍንቻን መሸፈን፣

·         የእጅ ንፅህናን መጠበቅ፦ ይህ ጉንፋንንና ሊሎች ኢንፌክሽኖችን ለመከላከል ይረዳል

·         እናቶች ልጆችን ጡት እንዲያጠቡ መምከር፦የእናት ጡት ወተት ከጆሮ ኢንፌክሽን የሚከላከሉ አንቲቦዲዎችን ይዟል። ስለሆነም ቢያንስ ለመጀመሪያዎቹ ስድስት ወራት ለጆችን ጡት ማጥባት ያስፈልጋል።

·         ሲጋራ ከማጨስ መቆጣብ ወይም ከሲጋራ ጭስ መራቅ

·         ልጅዎ ጡጦ የሚጣባ ከሆነ በተኛበት ማትባት አይመከርም፤ ይልቁኑ ልጅዎን ሲያጡቡ ከፍ አድርጎ መያዝ ያስፍልጋል።

·         ለጨቅላ ህጻን የእንጃራ እናት ወይም ፔሲፋየር ከመስጠት ይቆጠቡ

ሊደረግ የሚችል ህክምና

·         ፀረ-ባክቲሪያ መድሃኒት

·         የህመም ማስታገሻ


Share with: