094 046 4646/0940 565656    
info@sainturaelclinic.com
Follow Us:

View Blog

አለም አቀፍ የኤች አይቪ ኤድስ ቀን

ዛሬ ህዳር 22 ወይም ዲሴምበር 1 ቀን አለም አቀፍ የኤች አይቪ ኤድስ ቀን ሲሆን በመላ አለም ተከብሮ ይዉላል።

ስለ ኤች አይቪ ኤድስ እዉነታዎች

·         ኤች አይ ቪ እስካሁን  በአለማችን 36.3 ሚሊዮን [27.2-47.8 ሚሊዮን] ህይወት በመቅጠፍ   ዋነኛ የአለም የህብረተሰብ ጤና ጉዳይ ሆኖ ቀጥሏል።

·         ኤች አይቪ ኤድስን ሙሉ በሙሉ ማዳን የሚችል መድኃኒት የለም። ነገር ግን ኤችአይቪን ጨምሮ ተጓዳኝ ህማሞችን የመከላከል፣የምርመራ፣የህክምና እና እንክብካቤ ተደራሽነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ በመምጣቱ ኤችአይቪ ኢንፌክሽንን መቆጣጠር የሚቻልና  ሥር የሰደደ የጤና ችግር እንዲሆን እንዲሁም ከኤችአይቪ ጋር የሚኖሩ ሰዎች ረጅም እና ጤናማ ህይወት እንዲመሩ አስችሏቸዋል።

·         በ2020 መጨረሻ ላይ  በዓለማችን 37.7 ሚሊዮን (30.2-45.1 ሚሊዮን) ሰዎች ከኤችአይቪ ጋር ይኖራሉ ተብሎ የሚገመት ሲሆን ከሁለት ሦስተኛው በላይ የሚሆኑት (25.4 ሚሊዮን) በአፍሪካ አህጉር ይገኛሉ።

·         በ2020፣ 680 000 [480 000–1.0 ሚሊዮን] ሰዎች ከኤችአይቪ ጋር በተያያዙ ምክንያቶች ህይወታቸዉ ያለፈ ሲሆን 1.5 ሚሊዮን [1.0-2.0 ሚሊዮን] ሰዎች በኤች አይ ቪ ቫይራስ ተይዘዋል።

·         እ ኤ አ በ2021 በኢትዮጵያ  616,105 ሰዎች ኤች አይቪ ቫይረስ በደማቸዉ ይኖራል ተብሎ ይገመታል( PEPFAR)

·         በሀገራችን የኤች አይቪ ኤድስ ስርጭት (ፕሪቫለንስ) 0.9 በመቶ ነዉ።

ኣራስዎን፣ቤተስብዎን እንዲሁም ማህበረሰቡን ከኤች አይቪ ኤድስ ወረርሽን ይጠብቁ!! የመ ህጎችን ያስታዉሱ!!

Share with: