የሽንት ቶሎ ቶሎ መምጣት ችግር አጋጥሞዎታል? ይህ የህመም ምልክት ሊሆን ስለሚችል የህክምና ባለሙያዎን ያማክሩ።
የሽንት ቶሎ ቶሎ መምጣት ማለት ሽንት በቀን፣ በሌሊት (nocturia) ወይም በሁለቱም ግዜ በድግግሞሽ ሲመጣና የሽንት መጠኑም በመደበኛ ወይም ከመደበኛ መጠን በታች ብዙ ጊዜ የመሽናት ፍላጎት ነው። ከሽንት ቶሎ ቶሎ መምጣት ጋር የሽንት ማጣደፍ ሊኖር ይችላል። የሽንት ቶሎ ቶሎ መምጣት በየትኛዉም ደረጃ ያለ የሽንት መተላልፊያ ስርዓትን ሲጠቃ ሊከሰት ይችላል። የሽንት መተላለፊያ ስርዓት የሚያጠቃልለዉ ኩላልት፣ ከላሊትን ከፊኛ ጋር የሚያገናኘዉ ቱቦ( ዩሬተር)፣ፊኛ፣ ከፊኛ ሽንትን ከሰዉነት ዉጭ የሚያስወጣዉ ቱቦ( ዩሬትራ) ናቸዉ።
ከሽንት ቶሎ ቶሎ መምጣት ጋር ሊገናኙ ከሚችሉ ምክንያቶች ዉስጥ
· የፊኛ ኢንፌክሽን፣ ህመም፣ አደጋ ወይም መቆጣት
· የሽንት መመረት ሂደት ሊጨምሩ የሚችሉ ሁኔታዎች መኖር
· የፊኛ ተግባርን ሊያዉኩ የሚችሉ በጡንቻዎች፣ ነርቮች ወይም ሌሎች ሕብረ ሕዋሳት ላይ የሚደረጉ ለውጦች
· የካንሰር ህክምናዎች
· የሸንትን መጠን ሊጨምሩ የሚችሉ መድሃኒቶችና መጠጦች ናቸዉ።
በተደጋጋሚ የሽንት መሽናትዎን በሚያመጣው ላይ በመመስረት፡ ሌሎች የሽንት ችግሮች ሊያጋጥምዎት ይችላል፡ ለምሳሌ፡-
· ሽንት በሚሸኑበት ወቅት ህመም ወይም ምቾት ማጣት
· ሽንት ለመሽናት መጣደፍ(ሽንት ማጣደፍ)
· ሽንት ለመሽናት መቸገር( ሽንት ሲሸኑ መቸገር)
· ሽንት ማምላጥ
· ያልተለመደ የሽንት ቀለም መቀየር ናቸዉ።
የሽንት ቶሎ ቶሎ ወይም በተደጋጋሚ አንዲመጣ ከሚያደርጉ መንሴዎች ዉስጥ የሚከተሉትን ሊያጠቃልል ይችላል።
· የኩላሊት ኢንፌክሽን
· የሽንት መተላለፊያ ስርዓት ኢንፌክሽን
· የፊኛ ጠጠር
· እርግዝና
· ለሽንት ማሸኛ የሚሰቱ መድሃኒቶች
· የፕሮስቴት ዕጢ መቆጣት
· የስኳር ህመም
· የሽንት መተላለፊያ ቱቦ ጥበት
· የሽንት መቆጣጠር ችግር
· መጨናነቅ ( አንዛይቲ)
· የፕሮስቴት ዕጢ ማደግ ( በወንዶች ላይ)
· አጠቃላይ ፈሳሾችን፣ አልኮል ወይም ካፌይን ከመጠን በላይ መጠጣትና የመሳሰሉትን ያጠቃልላል።