የሀሞት ጠጠር በሀሞት ከረጢት ወስጥ የሚፈጠር ነዉ። የሀሞት ከረጢት በቀኝ የሆድ ክፍል ከኩበት ስር የምትገኝ የአካላችን ክፍል ናት። የሀሞት ከረጢት ለምግብ መፈጨት የሚያገለግለዉን ሀሞት አጠራቅሞ የሚይዝ ነዉ።
የህመም ምልክቶች
የሀሞት ጠጠር ምንም አይነት የህመም ምልክት ላይኖረዉ ይችላል። የሀሞት ጠጠር ወደ ሀሞት መተላለፊያ ቱቦ ዉስጥ ገብቶ ተቀርቅሮ ከቀረ የሚከተሉት የህመም ምልክቶች ሊታዩ ይችላሉ።
· በቀኝ የላይኛዉ የሆድ ክፍልዎ አካባቢ በድንገት ጀምሮ እየተባባሰ የሚሄድ ህመም መከሰት
· በጀርባ በኩል በሁለቱ ትከሻዎ መሃል ህመም መከሰት
· በቀኝ ትከሻዎ ላይ ህመም መከሰት
· ድንገተኛና በፍጥነት የሚባባስ ህመም በሆድዎ መሃል ከደረት አጥንት ስር ህመም መሰማት
· ማቅለሽለሽ ወይም ማስታወክ ናቸዉ።
የሀሞት ጠጠር ህመም ከብዙ ደቂቃዎች እስከ ጥቂት ሰዓታት ሊቆይ ይችላል።
መንሴዎች
የሀሞት ጠጠር እንዲፈጠር የሚያደርገው ምን እንደሆነ ግልጽ አይደለም። የህክምና ባለሙያዎች የሀሞት ጠጠር በሚከተሉት ምክንያቶች ሊከሰት ይችላል ይላሉ፦
· በሀሞቱ ዉስጥ የበዛ የስብ መጠን ሲኖር፦ በተለምዶ የእርስዎ ሀሞት በጉበትዎ የሚወጣውን ኮሌስትሮል ለመሟሟት በቂ ኬሚካሎችን ይይዛል። ነገር ግን ጉበትዎ ሀሞቱ ሊያሟሟዉ ከሚችለው በላይ ኮሌስትሮል ካመረተ ወይም ካመነጨ ትርፉ ኮሌስትሮል ወደ ክሪስታል እና በመጨረሻም ወደ ድንጋይ በመቀየር የሀሞት ጠጠር ሊፈጠር ይችላል።
· ሀሞትዎ ከመጠን ያለፈ ቢሊሩቢን ከያዘ፦ ቢሊሩቢን ሰውነትዎ ቀይ የደም ሴሎችን ሲሰባበሩ የሚመረት ኬሚካል ነው። ከመጠን በላይ የሆነው ቢሊሩቢን ለሀሞት ጠጠር መፈጠር አስተዋጽኦ ያደርጋል።
· የሀሞት ከረጢቷ በትክክለኛዉ ሁኔታ ሀሞት የማያስወጣ ከሆነ፦ የሀሞት ከረጢቷ ሀሞትን በሙሉ የማታስወግድ ከሆነ ሀሞቱ ከመጠን በላይ ይወፍራል፤ ይህም ለሀሞት ጠጠር መፈጠር ምክንያት ይሆናል።
የሀሞት ጠጠር አይነቶች
· የኮሌስትሮል ጠጠሮች፦ይህ በብዛት ከሚከሰት የሀሞት ጠጠር ሲሆን ቢጫማ መልክ አላቸዉ። እነዚህ የሀሞት ጠጠሮች በዋናነት ካልሟሙ ኮሌስትሮሎች የተሰራ ሲሆን ሌሎች ነገሮችንም ሊይዙ ይችላሉ።
· ቀለማማ( የተቀለሙ) የሃሞት ጠጠሮች፦ ይህ ጠቁር ወይም ብራዉን መልክ ያላቸዉ ሲሆን የሚፈጠሩት ሀሞት ቢሊሩቢን ኬሚካልን ከመጠን በላይ ሲይዝ ነዉ።