አጋላጭ ምክንያቶች
ለሃሞት ጠጠር መፈጠር አጋላጭ የሆኑ የተለያየ ምክንያቶች ያሉ ሲሆን ከነዚህም ዉስጥ፦
· ሴት መሆን
· እድሜዎ ከ40 ዓመት በላይ ሲሆን
· የሰዉነት ክብዳትዎ ከመጠን በላይ ወይንም ወፍራም መሆን
· እንቅስቃሴ የማያደርጉ ከሆነ
· ነፍሰጡር መሆን
· የስብ ይዘታቸዉ ከፍተኛ የሆኑ ምግቦችን አብዝቶ መመገብ
· የፋይበር ይዘታቸዉ አነስተኛ የሆኑ ምግቦችን የሚመገቡ ሰዎች
· በቤተሰብ ዉስጥ የሀሞት ጠጠር ያለበት ሰዉ ካለ
· የስኳር ህመም ካለዎ
· እንደ ሊኮሚያና ሲክልሴል አኒሚያ አይነት የደም ሴሎች ችግር ያለባቸዉ ሰዎች
· የሰዉነት ክብደትዎን በፍጥነት መቀነስ
· እንደ የወሊድ መቆጣጠሪያ ያሉ ኢስትሮጂን ያላቸዉ መድሃኒቶችን የሚወስዱ ሰዎችኝና
· የጉበት በሽታ ያላቸዉ ሰዎች ናቸዉ።
ሊያመጣዉ የሚችለዉ የጎንዮሽ ጉዳት
· የሀሞት ከረጢት መቆጣት፦ በሀሞት ከረጢት አንገትና የሀሞት መተላለፊያ ቱቦ ላይ ተቀርቅሮ የሚቀር የሀሞት ጠጠር የሀሞት ከረጢት እብጠትና መቆጣት (cholecystitis) ሊያስከትል ይችላል። ይህ የሀሞት ከረጢት እብጠትና መቆጣት ከባድ ህመም እና ትኩሳት ሊያስከትል ይችላል።
· የሀሞት መተላለፊያ ቱቦ መዘጋት፦ የሀሞት ጠጠር ከጉበትና ከሀሞት ከረጢት ወደ አንጀት ሀሞት የሚወስደዉን ቱቦ ሊዘጋዉ ይችላል። በዚህም የተነሳ ከፍተኛ ህመም፣ የአይንና ሰዉነት ቢጫ መሆንና የሀሞት መተላለፊያ ቱቦ ኢንፌክሽን ሊያመጣ ይችላል።
· የቆሽት ቱቦ መዝጋት፦ በሀሞት ጠጠር ምክንያት የቆሽት ቱቦ መዘጋት ከተፈተረ ለቆሽት መቆጣት መንሴ ሊሆን ይችላል።
· የሀሞት ከረጢት ካንሰር፦ የሀሞት ጠጠር ታሪክ ያላቸው ሰዎች ለሀሞት ከረጢት ካንሰር የመጋለጥ እድላቸው ከፍ ያለ ነው። ነገር ግን የሃሞት ፊኛ ካንሰር በጣም አልፎ አልፎ የሚከሰት ነው በብዛት የሚከሰት አይደለም)።
የሀሞት ጠጠርን መከላከል
· የፋይበር ይዘታቸዉ ከፍተኛ የሆኑ ምግቦችን መመገብ፦ አትክልት፣ ፍራፍሬና ጥራጥሬ ምግቦችን በደንብ ይመገቡ
· ጤናማ የሰዉነት ክብደት እንዲኖርዎ ያድርጉ፦ ከመጠን ያለፈ ውፍረትና ከመጠን በላይ የሰዉነት ክብደት ለሃሞት ጠጠር የመጋለጥ እድልን ይጨምራል። የሀሞት ጠጠርን ለመከላከል የሰዉነት ክብደትዎን ያመጣጥኑ።
· የሰዉነት ክብደትዎን ባንዴ ሳይሆን ቀስ እያሉ ይቀንሱ; -የሰዉነት ክብዳት ለመቀነስ የሚያስቡ ከሆነ ባንዴ ሳይሆን ቀስ በቀስ ለመቀነስ ይሞክሩ።
· የመመገቢያ ሰዓትዎን አለመዝለል፦ በየቀኑ በተለመደው የምግብ ሰዓትዎ ጠብቀዉ ይመገቡ እንዲሁም የመመገቢያ ሰጣትዎንና ምግብን መዝለል የሃሞት ጠጠር ተጋላጭነትን ይጨምራል።