094 046 4646/0940 565656    
info@sainturaelclinic.com
Follow Us:

View Blog

ቅድመ-ስኳር (Prediabetes)

ቅድመ የስኳር  ማለት በደምዎ ዉስጥ ከተለመደው የደም ስኳር መጠን በላይ ከፍ ያለ የስኳር መጠን ሲኖር የሚከሰት የስኳር  ደረጃ ማለት ነው። ይህም ማለት በደም ውስጥ ያለው የስኳር መጠን ከወትሮው ከፍ ያለ ነገር ግን አንድ ሰዉ    የስኳር ህመም ያለበት ደረጃ (አይነት 2 የስኳር ህመም) ያልደረሰና ከባድ የጤና ችግር ሊያመጣ የሚችል ነው።

ቅድመ-ስኳር ካለዎ የስኳር በሽታ የረጅም ጊዜ ጉዳት በተለይም በልብዎ፣ በደም ሥሮችና ኩላሊትዎ ላይ ምናልባት እየጀመረ ሊሆን ይችላል። አስቀድመን መከላከል ካልቻልን ከቅድመ-ስኳር በሽታ ወደ ዓይነት 2 የስኳር በሽታ መቀየር ወይም ማደግ የማይቀር ነገር ይሆናል።

ጤናማ ምግቦችን መመገብ፣ የአካል ብቃት እንቅስቃሴን የእለት ተእለት እንቅስቃሴዎ አካል ማድረግና ጤናማ የሰዉነት ክብደት መጠን እንድኖርዎ ማደረግ የደምዎን የስኳር መጠን ወደ መደበኛው እንዲመልስ ይረዳል።

አንድ ሰዉ ቅድመ-ስኳር ችግር አለበት የሚባለዉ የሚከተሉትን ሲያሟላ ነዉ

·         ተፁሞ የሚሰራዉ የስኳር መጠን፦ ከ 100ሚሊግ/ዴሲሊትር እስከ 125 ሚሊግ/ዴሲሊትር ሲሆን

·         ሳይፆም ወይም ተበልቶ የሚሰራዉ የደም የስኳር መጠን፦ ከ 140ሚሊግ/ዴሲሊር እስከ 199ሚሊግ/ዴሲሊትር ከሆነ

·         የሶስት ወር አማካይ የስኳር መጠን የሚለካዉ ወይም ሄሞግሎቢን ኤዋን ሲ( HgA1c) መተን፦  ከ 5.7%- 6.4% ከሆነ የቅድመ-ስኳር ችግር አለ እንላለን።

የህመም ምልክቶች

ቅድመ-ስኳር ችግር ያለባቸዉ ሰዎች ምንም አይነት የህመም ምልክቶች ላይኖራቸዉ ይችላሉ። ነገር ግን ምልክት ከታየ ለቅድመ-ስኳር በሽታ አንዱ ምልክት ሊሆን የሚችለው በአንዳንድ የሰውነት ክፍሎች ላይ የጠቆረ ቆዳ ነው። ጉዳት ሊደርስባቸዉ ከሚችልባቸዉ አካባቢዎች ዉስጥ አንገት፣ ብብት፣ ክርኖች፣ ጉልበቶችና አንጓዎች ሊያካትቱ ይችላሉ።

ከቅድመ-ስኳር በሽታ ወደ ዓይነት 2 የስኳር በሽታ መሸጋገሩን የሚጠቁሙ የተለመዱ ምልክቶች ዉስጥ የሚከተሉትን ያካትታሉ፦

·         የዉሃ ጥማት መጨመር

·         በተደጋጋሚ ሽንት መሽናት

·         ከመጠን ያለፈ ረሃብ

·         ድካም

·         የእይታ መደብዛዝ ናቸዉ።


Share with: