የተለያዩ ፍራፍሬዎችንና አትክልቶችን የያዘ የምግብ አመጋገብ ብዙ የጤና ጥቅሞችን ይሰጣል። ይህም የስኳር ህመም፣ ዉፍረትን ለመቀነስ፣ የልብ ህመምና አጠቃላይ ሞትን ለመቀነስ እንዲሁም ለጤናማ ቆዳና ፀጉር፣ ሃይል ወይም ጉልበት ለመጨመርና ክብደትን ለማስተካከል ይረዳል።
11 የአቮካዶ የጤና ጥቅሞች
1. በንጥረ ነገሮች የበለፀገ ነዉ።
አቮካዶ የቫይታሚን ሲ፣ ኢ፣ ኬ እና ቢ6 እንዲሁም የሪቦፍላቪን፣ ኒያሲን፣ ፎሌት፣ ፓንታቶኒክ አሲድ፣ ማግኒዚየምና ፖታሲየም ምንጭ ነው። በተጨማሪም ሉዩቲን፣ቤታ ካሮቲን እና ኦሜጋ -3 ፋቲ አሲድ ይሰጣል።አቮካዶ ከፍተኛ መጠን ያለው ጤናማና ጠቃሚ የሆኑ ቅባቶችን በውስጡ የያዘ ሲሆን ይህም አንድ ሰው በምግብ መካከል የመጥገብ ስሜት እንዲሰማዉ ያደርጋል። ስብን መመገብ የካርቦሃይዲሬት በሰዉነት ዉስጥ መሰባበርን በመቀነስ በደም ውስጥ ያለው የስኳር መጠን እንዲረጋጋ ያደርጋል።
2. ለልብ ጤንነት
በያንዳንዱ 100 ሚልግራም አቮካዶ 76 ሚሊግራም ቤታ ሳይቶስትሮል ተብሎ የሚጠራው የተፈጥሮ እፅዋት ስቴሮል ይይዛል። ቤታ ሲቶስተሮልንና ሌሎች የእፅዋት ስቴሮሎችን አዘውትሮ መውሰድ ጤናማ የኮሌስትሮል መጠን እንዲኖር ስለሚረዳ ለልብ ጤና ጠቃሚ ነው።
3. ለአይን እይታ ጠቃሚ ነዉ
አቮካዶ በአይን ቲሹ ውስጥ የሚገኙትን ሉቲንና ዛንቲን የተባሉ ሁለት ፋይቶኬሚካሎችን ይዟል። እነዚህም አነቲኦክሲዳንት ስላላቸዉ አይንን ከፀሃይ ጨረረር ጉዳት ጨምሮ ከሌሎች አደጋዎችም ይካላከላል።
4. የአጥንት መሳሳትን ለመከላከል ይራዳል፦ አቮካዶ ከፍ ያለ የቫይታሚን ኬ ምንጭ ነዉ። ይህ ብዙዉን ጊዜ ባይጠቀስም ለአጥንት ጤንነት ጠቃሚ ነዉ። በቂ ቪታሚን ኬን መውሰድ የካልሲየምን ከአንጀት መመጠጥንና በመጨመርና የካልሲየምን ከሰዉነት ከሽንት ጋር መውጣትን በመቀነስ የአጥንትን ጤንነት ይደግፋል።
5. የፅስን ጤንነት ለመደገፍ ይረዳል፦ ፎሌት ለጤናማ እርግዝና አስፈላጊ ነው። በቂ መጠን ያለው አመጋገብ የፅንስ መጨንገፍና የነርቭ ስርዓት ችግርን ይቀንሳል። አንዲት ነፍሰጡር አናት በቀን እስክ 600 ማይክሮግራም ፎሌት መመገብ አለባት።
6. የምግብ መፈጨትን ያሻሽላል፦ አቮካዶ ከፍተኛ ፋይበር አለው። ተፈጥሯዊ ፋይበር የያዙ ምግቦችን መመገብ የሆድ ድርቀትን ለመከላከል፣ የአንጀት ጤንነትን ለመጠበቅና የአንጀት ካንሰር ተጋላጭነትን ለመቀነስ ይረዳል።
7. የድብታ ተጋላጭነትን ይቀንሳል፦ አቮካዶ ጥሩ የፎሌት ምንጭ ሲሆን ፎሌት ሄሞሲስቲን በሰዉነታችን ዉስጥ ከመጠን በላይ እንዳይጠራቀም ስለሚያደርግ ድብታን ለመቀነስ ይረዳል።
8. በተፈጥሮ መርዛማ ነገሮችን ለማርከስ( ዲቶክሲፊኬሽን) ይረዳል፦ በቂ ፋይበር አዘውትሮ መመገብ የአንጀት እንቅስቃሴን ጥሩ እንዲሆን ያደርጋል ፤ ይህም መርዛማ ንጥረ ነገሮች በሰገራና በሃሞት በኩል ከሰዉነት ለማስወገድ ይረዳል።
9. የአጥንት መገጣጠሚያ መቆጣት ( ኦስቲኦአርትራይትስ) ለመቀነስ ይረዳል፦ አቮካዶ፣ አኩሪ አተርና አንዳንድ ሌሎች የእፅዋት ምግቦች ሳፖኒን ይይዛሉ። እነዚህ ንጥረ ነገሮች በጉልበትና በዳሌ መገጣጠሚያ መቆጣት ምልክቶች ላይ አዎንታዊ ተጽእኖ ሊኖራቸው ይችላል
10. ፀረ-ባክቴሪያ ባህሪ አለዉ፦ አቮካዶና የአቮካዶ ዘይት ፀረ-ተሕዋስያን ባህሪያት ያላቸውን ንጥረ ነገሮች ይይዛሉ.
11. ስር ከሰደደ ህመም ይከላለላል፦ በአቮካዶ ውስጥ የሚገኙት ጤናማ የስብ አይነቶች( ሞኖሳቹሬትድ ፋቲ አሲድ) እንደ የልብና የደም ሥር (cardiovascular) በሽታ ያሉ ሥር የሰደዱ በሽታዎችን ለመከላከል ጠቃሚ ናቸዉ።