ዓይነት 2 የስኳር በሽታ የመያዝ እድልን የሚጨምሩ ነገሮች ለቅድመ-ስኳር በሽታ ተጋላጭነትን ይጨምራሉ። እነዚህ ምክንያቶች የሚከተሉትን ያካትታሉ:
· የሰዉነት ክብደት፦ ከመጠን በላይ መወፈር ለቅድመ-ስኳር በሽታ ቀዳሚ አጋላጭ ነው።
· አመጋገብ፦ ቀይ ስጋና የተቀነባበረ ስጋን መመገብ እንዲሁም በስኳር የተሰሩ ጣፋጭ መጠጦችን መጠጣት ለቅድመ-ስኳር በሽታ ተጋላጭነት ከፍተኛ አስትዋኦ ያደርጋሉ። በፍራፍሬ፣ በአትክልት፣ በለውዝ፣ በጥራጥሬና በወይራ ዘይት የበለፀገ አመጋገብ ለቅድመ-ስኳር በሽታ ተጋላጭ የመሆን እድል ዝቅተኛ ነው።
· እንቅስቃሴ-አልባ የሆነ አኗኗር፦ የአካል እንቅስቃሴዎ ባነሰ ቁጥር ለቅድመ-ስኳር በሽታ የመጋለጥ እድልዎ ከፍ ይላል። የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ የሰዉነትዎን ክብደት እንዲቆጣጠሩ ይረዳዎታል፤ ስኳርን ለሀይል/ጉልበት እንዲቃጥል ያደርጋሉ፤ እንዲሁም ሰውነት ኢንሱሊንን በብቃት እንዲጠቀም ያደርጋል።
· እድሜ፦ ምንም እንኳን የስኳር በሽታ በማንኛውም እድሜ ሊከሰት ቢችልም ዕድሜዎ ከ45 አመት በኋላ ለቅድመ-ስኳር በሽታ የመጋለጥ እድሉ ይጨምራል
· በቤተሰብ ዉስጥ የስኳር ህመም መኖር፦ ዓይነት 2 የስኳር በሽታ ያለበት ወላጅ ወይም ወንድም ወይም እህት ካለዎት ለቅድመ-ስኳር በሽታ የመጋለጥ እድሎት ይጨምራል
· የእርግዝናዎ ወቅት የስኳር በሽታ መኖር፦. በእርግዝና ወቅት የስኳር በሽታ ካለብዎ (የእርግዝና የስኳር በሽታ) እርስዎ እና ልጅዎ ለቅድመ-ስኳር በሽታ የመጋለጥ እድል ከፍተኛ ነው።
· ፖሊሲስቲክ ኦቫሪያን ሲንድሮም፦ ይህ ችግር ያለባቸዉ ሰዎች ለቅድመ ስኳር ችግር የመጋለት ዕድላቸዉ ከፍተኛ ነዉ።
· የአንቅልፍ ችግር፦ ኦብስትራክቲቭ ስሊፕ አፕኒያ የሚባለዉ የእንቅልፍ ችግር ያለባቸዉ ሰዎች ለቅድመስኳር ችግር የመጋለጥ ዕድላቸዉ ከፍተኛ ነዉ።
· ሲጋራ ማጨስ፦ ማጨስ የኢንሱሊን ሬዚስታንስን ይጨምራል። ይህም ለቅድመስኳር ችግር ይዳርጋል።
· የወገብ መጠን፦ የወገብ መጠን ከፍ ያለ መጠን ያላቸዉ ሰዎች ለኢንሱሊን ሆርሞን መስራት መቀነስ( ኢንሱሊን ሬዚስታንስ) ችግር ይዳረጋሉ። የኢንሱሊን የመስራት አቅም መቀነስ ችግር አየጨመረ የሚያደርጉት ለወንዶች የወገብ መጠናቸዉ 101.6ሳንቲሜትር በላይና፣ ለሴቶች ከ88.9 ሳንቲሜትር በላይ ሲሆኑ ነዉ።
የጎንዮሽ ጉዳቶች
ቅድመ ስኳር ከሚያመጣቸዉ ነገሮች ዉስጥ ዋናዉ ወደ አይነት ሁለት የስኳር አይነት መቀየር ሲሆን በተጨማሪም ወደ አይነት ሁለት የስኳር አይነት በይቀየርም እንኳ ሳይታወቅ በድንገተኛ የልብ ችግርና ኩላሊቶችን ሊጎዳ ይችላል። ቅድመ ስኳር ችግር ወደ አይነት ሁለት የስኳር አይነት ከተቀየረ በኋላ ሊከሰቱ የሚችሉ የጎንዮሽ ጉዳቶች የሚከተሉትን ሊያጠቃልል ይችላል፦
· የደም ግፊት መጨመር
· የስብ መጠን ( ኮሌስትሮል) መጨመር
· የልብ ህመም
· ስትሮክ
· የኩላሊት ህመም
· የነርቭ መጎዳት
· የደም ቧንቧ ችግሮችና የእግር መቆረጥ ናቸዉ።
መከላከል
ጤናማ የኗኗር ዘይቤን መከተል ቅድመ ስኳር ችግርን ለመከላከልna ወደ አይነት ሁለት የሚያደርገዉን ለዉጥ ያስቀራል።
· ጤናማ ምግቦችን ይመገቡ
· የአከል ብቃት እንቅስቃሴ በቀን ቢያንስ ለ30 ደቂቃዎችና በሳምንት ለ5 ቀናት ያድርጉ
· ክብደትዎ ከመጠን ያለፈ ከሆነ ይቀንሱ
· የደም ግፊትዎንና የሰዉነት የስብ መጠንዎን(ኮሌስትሮልዎን) ይቆጣጠሩ
· ሲጋራ ከማጨስ ይቆጠቡ።